እንቢ ለዘረኝነት እልቂት በስሜት አንነዳም!! ( አቶ አሰገደ ገ/ስላሴ ከመቐለ -ለቃሊቲ ፕሬስ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በትግራይ ክል በሁሉም የዞን ፣የወረዳ ከተሞች ህገመንግስታች ተጥሷል በሚል ሞፎከርና ሌሎች ጥያቄዎች ያሉበት ለመጭው ቅዳሜ እና እሁድ ሰላላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ውስጥ ለውስጥ ሲነገር ፣ ሲታወጅ ሰንብቶ ነበር።ከዛሬ ቀን ከሰአት በኃላ ደግሞ እነ የአግአዝያን አስተባባሪ እና መሀሪ የውሀንስ ፣ የትግራይ ባለአደራ (ደመላሸ ) የሚባል በተሰው ታጋዮች ሰም ከ27 አመት በኃላ ረስተውት የኖሩ አሁን ስጨንቃቸው ለጥቅማቸው ሲሉ እነስብሀት ነጋ ፣ስዩም መስፍን በሌሎች የህወሓት ነባር አማራሮች አሁን በሞቱበት ሂወታቸው ያድነን እንደሆነ ብለው ያተዳራጀ ማህበር ፣ የህወሓት ጽፈት ቤት ሀላፊ አለም ገብረዋህድ የሚመራው የህወሓት መሪዎች ብቸኛ ተላላኪ ወጣት ሊግ ማህበር ኔት ወርክ እየተገላበጡ እያንቀሳቀሱት ያሉ ነው። መሀሪ የውሀንስ የሚባል በመቀሌ ዩንቨርሲቲ መሽጎ የፖለቲካ ሳይንስ አስተማሪ ነኝ ባዩ በማነኛውም ነገር እንደዝንብ ጥልቅ ብሎ በመግባት የዘረኝነት ማእበል እየፈጠረ በሀወሓት ውስጥ ይገባል ይወጣል እያጭጭበረበረ ዮነረ ። አሁንም አጋአዚያን ሆኖ የትግራይ የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ህዝቦች በአንድ ላይ ለመገንጠል እየተሯሯጠ የቆዬ ፣እንዳው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጱያ ሉአላዊ መሬት ለሸአብያ አሳልፎ ለመስጠት እየተሯሯጠ ቆይቶ ። እንደገና በአሁኑ ጊዜ የበአዴን እና የህወሓት መሪዎች ፈጥረውት ባሉት የስልጣን ችኩቻ ያን ተከትሎ በነ ደመቀ መኮነን ፣ ገዱ እንዳርጋቸው ፣ ሌሎች የባአዴን መሪዎች በትግሪያኖች ላይ እፈጸሙት ባሉት ግድያ አካል መጉዳል፣ ሀፍቲ መውረስ አጋጠሚ ተጠቅሞ ገናጣይ ሰራ እየተገበረ ይገኛልል ። ይሰው መቸ ይህ ብቻ አይደለም አሁን በግልጽ ትገሪያኖች ንገንጠል እያለ እየሰበከ ያለው ነው ግን ተቀባይነት የለውምና ። ይህ ሰው መሳይ አካል የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁር ሆኖ በህዝቦች የተፈጠረው ግርጭት ሳይንሳዊ መፍትሄ እንደመፈላለግ ፈንታ ህዝብ ለህዝብ ማጣረስ ሰይጣናዊ ተግባር የተጠናወተው መሆኑ ተረድታችሁ አገር ወዳድ ወገኖች ብትመክሩት የተሻለ ነበር ።

ይህ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዚሁ አንድ ወር ብቻ የህወሓት መሪወች ሁለት ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ የተላያዬ አላማ ይዘው ሰላማዊ ሰልፊ ለማድረግ አውጀው ሁለቱም ጊዜ በህዝብ ተቃውሞ ምክንያት አልተደረጉም ።

አሁን ደግሞ ለሀምሌ 15 /11 /2010 ዓ ም ተቀይራል ።

በሌላ በኩል ሰላማዊ ሰልፉ ማነው እየተጣራው?
በአለም ገብረዋህድ ? በዶክተር ደብረጽዬን ?በአክሱም እና በፕላኔት ሆቴሎች መሸገው በስብሰባ ተጠምደው ያሉ የህወሓት ፣የበአዴን ፣ የኦሆደድ ፣የደሂደን ከስልጣን የተወገዱ ወይ በጥሮታ የተወገዱ የድሮ የኢህአደግ ነባር አማራሮች ???
የአጋዝያን ተጠሪ መሓሪ የውሀንስ ?ወይ በባለ አደራ ( ደም መላሽ ) ፤

መልሱ ዶክቶር ደብረጽዮ እና ከነዚ ህ ወስጥ ያልተጠቀሱ ጓዶቹ አውጥተሀ ሌሎችም ግን ለትግራይ ህዝብና በባአዴን መሪውች አስተባባሪነት በክልል ሰወስት ህዝቦች በፈጸመው ኢህገመንግስታዊ ተግባራት ተቆርቁረው ሳይሆን የራሳቸው ስልጣንና ክብር ለመመለስ እሚያደርጉት ያሉ መንፈራገጥ ነው።

በዚህ ላይ የጎንደር፣የጎጃም ፣ የወሎ በበታችነት ስሜት በተዘፈቁት የበአዴን መሪዎች ፣ተጠቃሚ ካድሬዎቻቸው ፣እንዲሁም በነሱ የመልካም አሰተዳዳር ጉድለት ምክንያ ያደኸዩዋቸው ስራጥ ወጣቶች ፣ድርየውች እየተነዳችሁ ስትራተጅካዊ ወንድማችሁ የሆነው ዜጋችሁ ኢትዮጱያ የሆነው የትገራይ ህዝብ ሲጎዳ ሲወረሰ ሲሞት ፣በውሼት ውንጀላ ሲታሰር እያያችሁ ዝምታ መምረጣችሁ አሳዛኝ ክስተትነው።

አንድ ሀቅ ልንገራቹሁ የትግራይ ህዝብ በወንድሞሞቹ ትግሪያኖች ላይ አደጋ ሲደርስ ዝም ማለቱ ፣አቅም አጥቶ፣ ፈርቶ፣ በኃላ ሆኖ ለጥቅሙ ሲል በወንድሙ የክልል ሰወስት ዘርአዊ ፍጅት እንዲፈጽም የሚገፏፉት ሀይሎች የሉም ማለት አይደለም ።ከሁለት አመት በፊትም ፣ አምናም ፣አሁንም የሚገፈፉት አሉ ።
የትግራይ ህዝብ ጦርነት ያውቃል ወደ ጦርነት ከገባ እደሚያሸንፍ ያውቃል ለወታደራዊ ስልጠናም ጊዜ አይፈጅለትም ። ግን የትግራይ ህዝብ ኢትዮጱያዊ ሳይሆን ይህህዝብ ኢትዮጱያ ነው ኢትዮጱያዊ ዜጋ መሆን ሱዳናዊ ፣ኬኒያዊ ወይ ዓረባዊ ተሰዶ መጥቶ ጊዜው ጠብቆ ኢትዮጱያዊ ዜጋ ይሆናለ ። ይህ ህዝብ ግን ኢትዮጱያ ስለሆነ የኢትዮጱያ አንድነት ይገነባል እንጅ ጥቅማቸው በተነካ መሪዎች አይነዳም ። ይህ ስላችሁ የትግራይ ህዝብ ሀቀኛ ኢትዮጱያ የሆነ ኢትዮጱያ ህዝብ በሚገባ ያውቀዋል ።
የትግራይ ህዝብ በስሜት ለዘረኝነት እልቂት አይነዳም!!
አኛ ትላንትም ኢትዮጱያ ዛሬም ነገም ኢትየጲያ ነን!!
ከአስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
28 /10 20 10

 

Share.

About Author

Leave A Reply