Thursday, January 17

እንኳን የመሶቡን የእጄን ተውኩላችሁ! ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

እቴጌ ጣይቱ ቡጡል የኢትዩጵያ ንጉሠ ነገሥት ሚኒሊክ ሁለተኛው

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በ1998 እንደ ኢትዩጵያዊያን አቆጣጠር በመኃል አራዳ በፒያሣ ከተማ ውስጥ ተሰራ፡፡ እቴጌ ጣይቱ ቡጡል (በ1851 ተወልደው በ1918 አ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል) እቴጌ ጣይቱ በኢትዩጵያ የመጀመሪያውን ሆቴል የገነቡ ንግሥት ናቸው፡፡ ሆቴሉ እንግዶችን በዘመናዊ መንገድ ማስተናገድ የቻለ በዘመኑ ብቸኛ በመሆን ለሆቴል ኢንደስትሪው ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ለመሆን በቅቶል፡፡ በሆቴሉ ባሉት አንድ መቶ ሠላሳ አራት የመኝታ ክፍሎች፣ የባህር ማዶ እንግዶች፣ አገር ጎብኝዎችና፣ዲፕሎማቶች ተሰተናግደውበታል፡፡ እቴጌ ጣይቱ ቡጡል፣የኢትዩጵያ ንጉሠ ነገሥት ሚኒሊክ ሁለተኛው ሚስት ናቸው፡፡በኢትዩጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንድስትሪ ኪነ-ህንፃ ግንባታ በሃገራዊ ባህል ከተገነቡ ዘመናይ ማራኪ ሆቴል ውስጥ የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ነሐሴ 1898 ዓ.ም የተቆቆመው ሆቶል ነው፡፡ ‹‹የኃለኛው ከሌለ ፣የፊተኛው የለም!›› ያለው ድምፃዊ ቴድሮስ ካሣሁን ለዚህ ነበር፡፡

ይህን የሃገር ቅርስ ሳናስመልስ ለእቴጌ ጣይቱ ኃውልት እናቁምላቸው፣ አናቁምላቸው ጠብ ብንገባ ምን ሊረባን!!! ለግማሽ ምዕተ አመት የአማራና ኦሮሞ ህዝብን በማጋጨት የኖሩ የህወሓት/ ኢህአዴግ  ፖለቲከኞች በትረ ሥልጣናቸውን ቆንጥጠው፣ ዜጎችን ገድለዋል፣ አስረዋል፣ አሰድደዋል እንዲሁም የሃገር ኃብት ዘርፈዋል፣ ከዚህም ውስጥ የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል አንዱ ነው፡፡ ይሄ ለውጥ የመጣው የአማራና ኦሮሞ ወጣቶች በተለይ ቄሮና ፋኖ የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን የሰለጠኑ ወጣቶች አርቆ አስተዋይነት የሁለቱን ህዝብ ፍቅር በማንገስ የኦሮሞ ደም ደማችን ነው! የአማራ ህዝብ ደም ደማችን ነው በማለት በከፈሉት መሠዋትነት የተገኘ ለውጥ መሆኑን ለሰከንድ ያህል መዘንጋት አይገባንም እንላለን፡፡ እቴጌ ጣይቱ ቡጡል የኢትዩጵያ ንጉሠ ነገሥት ሚኒሊክ ሁለተኛው አማራና የኦሮሞ ደም እንዳላቸው የታሪክ መዛግብት ያረጋግጣል፣ ስለዚህ የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች በህብረት የወደቁ ወጣቶች ሠማዕታት ኃውልት ማቆም እንዲሁም የእቴጌ ጣይቱ ቡጡል ኃውልት ይገነባሉ እንላለን፡፡ ችግሮቻችንን ሁሉም ነገር በዴሞክራሲያዊ መንገድ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት የመፍታት ጥበባችንን በማዳበር የዘር ግጭትና የጥላቻ ፖለቲካ አስወግደን ለውጡን ማስቀጠል አስፈላጊ ነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የጥላቻና የዘር ግጭት የሚያስነሱ ቅስቀሳዎች ሰለባ መሆን አይኖርብንም፡፡ በአቶ በረከት ስምኦን አጀንዳ ቀያሪነት አርባ ክንድ ፁሁፍ መፃፍ ከእኛ አይጠበቅም፣ በእራሳችን አጀንዳ ዙሪያ መሽከርከር ይኖርብናል፡፡

እቴጌ ጣይቱ ቡጡል የመጀመሪያው ዘመናዊና ታሪካዊ ሆቴል በሃገራዊ ጥበቦች ማለትም የዶርዜ ሃይዞ ጥበቦች ጋቢና ብልኮዎች፣ የሸክላ ስራዎች ዋንጫ፣ ድስት፣ ሰታቴ፣ እንስራ፣ ገንቦ ወዘተ የነበረበት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የቡና መስተንግዶ ለባህር ማዶ ሰዎች የቀረበበት ነበር፡፡ ብርቅዬና ድንቅዬ የእደ ጥበብ ወንበሮች፣ጠረጵዛዎች፣ አልጋዎች እንዲሁም የስጦታ እቃዎች፣ ያካተተ ነበር፡፡ የኢትዩጵያ የፆም ምግቦች መስተንግዶ ሆቴሉ በባህር ማዶ ጎብኝዎች ተፈላጊነትና በዘመኑ የዲፕሎማቶች ማረፍያ ሆቴል ነበር፡፡ ሆቴሉ በሃገር ውስጥ እቃዎች የተገነባ በመሆኑ የብዙ ቱሪስቶች መስህብ በመሆን ተወዳጂነት ያገኘ የህዝብ ኃብት ለህዝብ እስኪመለስ ድረስ በሆቴሉ ያለመጠቀም አድማ ሊጠራ ይገባል እንላለን፡፡ ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለምና ባለአግባብ የተሸጠ የሃገሪቱን ሃብት ማስመለስ የዚህ ወጣት ትውልድ ሃላፊነት ነው እንላለን፡፡

በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በደርግ አገዛዝ ስርዓት የተወረሱ መንግስታዊ ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘወወር በ1994 ዓ/ም በአዋጅ የተቆቆመ ድርጅት ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ (ስዬ አብርሃ ወንድም) 05/19/99እኤአ ለእህታቸው ባል አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአምስት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሽህ ብር (5,273,000 ) ሸጡላቸው፡፡ በኢትዩጰያ የመጀመሪያ የሆነውን ጥንታዊ ሆቴል የሃገር ሃብትና ቅርስ ሆኖ ሳለ በበህወሃት/ኢህአዴግ ታሪክን የማጥፋት የቆየ ደመኝነት ለዘመዳቸው እንዲሸጥ ተደረገ፡፡ ገዥው 35በመቶ 1,845,550 ብር ከፍለው ቀሪውን 3,427,450 ብር በአምስት አመታት ውስጥ በአመት  685,490 ብር እየከፈሉ ለመጨረስ ተስማምተው ቅርሱን በእጃቸው አስገቡ፡፡

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ጥር 3 ቀን 2007 እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር በ109 አመቱ በእሳት ተቃጠለ፡፡ A fire broke out on early Sunday morning 11 January 2015, and with the coopration of the Fire brigade, Government agencies, neighbors, guests and our staffs we have managed to save this historical building. We express our deepest gratitude to all who have supported us during this difficult time. We would like to announce that the hotel is partially operational (75 rooms are operational) and in due time we will restore it to its formal glory.

2014 እኤአ በአፍሪካ አስር ሃገራቶች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ጥናት መሠረት ከአንድ እስከ አስር ደረጃ አግኝተዎል፡፡አንደኛ ደረጃ ያገኘችው ናይጀሪያ ስትሆን 40 ዘመናዊ ሆቴል፣6,614 የመኝታ ክፍሎችና አማካኝ የክፍል ስፋት 165 ሜትር ካሬ እንዳላት ታውቆል፡ሁለተኛ ደረጃ ያገኘችው ሞሮኮ ስትሆን 29 ዘመናዊ ሆቴል፣4,828 የመኝታ ክፍሎችና አማካኝ የክፍል ስፋት 166 ሜትር ካሬ፡፡ ሦስተኛ ደረጃ ያገኘችው ግብፅ ስትሆን 15 ዘመናዊ ሆቴል፣4,703 የመኝታ ክፍሎችና አማካኝ የክፍል ስፋት 314 ሜትር ካሬ፡፡አራተኛ አልጀሪያ 15 ዘመናዊ ሆቴል፣3,172 የመኝታ ክፍሎችና 211ሜ/ካ አማካኝ የክፍል ስፋት፡፡አምስተኛ ደረጃ ሊቢያ 7 ዘመናዊ ሆቴል፣2,205 የመኝታ ክፍሎችና 315ሜ/ካ አማካኝ የክፍል ስፋት፡፡ስድስተኛ ቱኒሲያ 7 ዘመናዊ ሆቴል፣1,541የመኝታ ክፍሎችና 220 ሜ/ካ አማካኝ የክፍል ስፋት፡፡ሰባተኛ ደቡብ አፍሪካ 9 ዘመናዊ ሆቴል፣1,293 የመኝታ ክፍሎችና 144ሜ/ካ አማካኝ የክፍል ስፋት ፡፡ስምንተኛ ጋና 6 ዘመናዊ ሆቴል፣1,080የመኝታ ክፍሎችና 180 ሜ/ካ አማካኝ የክፍል ስፋት ፡፡ኢትጵያ ዘጠነኛ ደረጃ ስታገኝ ስድስት ዘመናዊ ሆቴል፣990 የመኝታ ክፍሎችና 165 ሜትር ካሬ አማካኝ የክፍል ስፋት፡፡በመጨረሻም  አስረኛ ደረጃ ሴኒጋል 5 ዘመናዊ ሆቴል 914 የመኝታ ክፍሎች እንዳሎቸው መረጃው አትቶል፡፡

‹‹የፕራይቬታይዜሽን››፣ የሆቴል ሚሊየነሮች!!!

‹‹ወርቅ የምትወልደውን ዝይ ገደልናት!!!››

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ይገኙ የነበሩ ስዕሎች ሰአሊው ማን ይሆን፣ የምታውቁ እባካችሁ አብራሩልን፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከናሽናላይዜሽን ወደ ፕራይቬታይዜሽን ሽግግር፡-እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከ1980 እስከ 2010 ዓ/ም የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት ማዘዋወር በምዕራባዊያን አገራቶች አዛዥነት በዓለም ባንክና አይኤምኤፍ ጋሻ ጃግሬነት ዓለም ዓቀፋዊ ክስተት በመሆን በኢትዮጵያም ተፈፃሚ ሆኖል፡፡ በሃገራችን ውስጥ ከመንግስት ዘርፍ ወደ ግሉ ዘርፍ መተላለፍና መሸጥ ዋነኛ ምክንያቶች መኃል፣ የገንዘብ አያያዝ ብክነትና ሙስና  በየግዜው እየጨመረ መሄድ፣ንብረቶቹን የማስተዳደር ብቃት ደካማነት በዚህም ምክንያት በየአመቱ የመንግስት ድጎማ  እየተደረገላቸው በኪሳራ መስራታቸው የሚል ነበር፡፡ በዓለም ዓቀፋ የገንዘብ ድርጅት ተቆምና በዓለም ባንክ ግዳጅና ተፅዕኖ የመንግስታዊ መዋቅር ስርዓት ማሻሻያ መርሃ-ግብር (structural adjustment program) ለማሻሻልና ለመቀየር የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት ማዘዋወር ዋነኛው ምክንያት ሆነ፡፡ የዓለም ዓቀፍ ፋይናንሻል  ኢንስቲቱሽን በተለይ  በታዳጊ አገሮች ላይ ትልቅ ጫና በመፍጠር የፕራይቬታይዜሽን መርሃ-ግብር ከመንግስታዊ መዋቅር ማሻሻያ ፕሮግራም ዋነኛ አካል እንደሆነ ተሰበከ፡፡

የወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት የተመቻቸለትን የዘረፋ ሁኔታ በማመቻቸት በሃገሪቱ የፕራይቬታይዜሽን ሽግግር በብቃትና  በግልፅነት ለማካሄድ አስፈላጊው ጊዜና ጥናት ባለመካሄዱ የተኮላሸ ለመሆን በቅቶል፡፡ በክንውኑም የወያኔ የቢዝነስ ድርጅቶችና ጥቂት ከበርቴዎች ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ያደረገ ሆኖል፡፡ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በወታደራዊው መንግሥት የተወረሱ መንግስታዊ ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ በ1994 ዓ/ም በአዋጅ ለማዘወወር የተቆቆመ ድርጅት ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ የመንግሥት ሆቴሎች ሽያጭ፣ በዝምድና በሙስና በጠባብ ዘረኝነት ስሜት አንዱን ለመጥቀም የወያኔ የንግድ ድርጅቶችንና ጥቂት ባለጸጎችን በፕራይቬታይዜሽን ስም ሚሊየነሮች ያደረጉት ሆቴሎቹን በርካሽ በመሸጥ ነበር፡፡ ዛሬ እነዚህ በርካሽ የተሸጡት የመንግሥት ሆቴሎች፣ ከመቶ እጥፍ በላይ ሊሸጡ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ፡፡ የፕራይቬታይዜሽን መርሃ-ግብር በሙስና የተጨማለቀ በመሆኑ የመርማሪ ኮሚሲዩን አቆቁሞ አስፈላጊው ምርመራ ማድረግ የአዲሱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች የአባቶቻችሁን የሙስናና ዝርፍያ በማጋለጥ ቃጣዩን ህይወታችሁን በነፃነት፣በእኩልነትና በፍትህ ለመኖር ታገሉ፡፡

የመንግስት የሆቴል ኢንተርፕራየዝ ሽያጭ ከ1994/95 እስከ 2003 ፕራይቬታይዝ የተደረጉ

(List of Privatized Stat Owned Hotels Enterprises from 1994/95 up to March 2003)

{1} ራንዴቩ ካፍቴሪያ3   የመንግስት ሆቴል በ06/25/97 ዓ/ም፣ለወ/ሮ እንይሽ አስራት የተሸጠበት ዋጋ 2,800,000.00 ሚሊዩን ብር

{2} አክሱም ሆቴል1 የመንግስት ሆቴል በ07/01/95 ዓ/ም፣ለኢትዩጵያ ትራቭል ኤክስፕሬስ የተሸጠበት ዋጋ 890,167.00 ሽህ ብር

{3} ፎገራ ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ07/03/00 ዓ/ም፣ ገዢ ጌትኮ ካንፓኒ( Geaitco.) የተሸጠበት ዋጋ 950,105.00 ሽህ ብር

{4} ወንዛዬ ሆቴል1 የመንግስት ሆቴል በ09/11/95 ዓ/ም፣  አማራ ዲቨሎፕመንት አሳሴሽን የተሸጠበት ዋጋ 500,000 .00 ሽህ ብር

{5} ተራራ ሆቴል4  የመንግስት ሆቴል በ12/02/95 ዓ/ም ፣ ገዢ አዲስ ፋና የተሸጠበት ዋጋ 617,480.92 ሽህ ብር

{6} ባህር ዳር ጊዩን1 የመንግስት ሆቴል በ07/04/95 ዓ/ም፣ለፉአንግ ቢውልዲንግ ኮንትራክተር የተሸጠበት ዋጋ 1,100,000.00 ሚሊዩን ብር

{7} ጣይቱ ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ05/19/99 ዓ/ም፣ዘ የሎ ፔጅ ለአቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም የተሸጠበት ዋጋ 5,273,000 ሚሊዩን ብር

{8} ግሸን ሆቴል(ጊዩን)@2  የመንግስት ሆቴል በ07/19/99 ዓ/ም ፣ ገዢ ወ/ሮ ይህደጋ ገብረስላሴ የተሸጠበት ዋጋ 12,527.15 ሽህ ብር

{9} ራስ ሆቴል (ደብረዘይት)1 የመንግስት ሆቴል በ09/04/96 ዓ/ም፣ ገዢ ሜድሮክ ኢትዩጵያ የተሸጠበት ዋጋ 8,027,302.23 ሚሊዩን ብር

{10} ራስ ግሪል1 የመንግስት ሆቴል በ07/19/99 ዓ/ም፣ ገዢ አዲስ ፋና የተሸጠበት ዋጋ 229,993.20 ሽህ ብር

{11} ላሊበላ ሬስትቶራንት1  የመንግስት ሆቴል በ09/26/95 ዓ/ም፣ ገዢ አይቤክስ ሆቴል የተሸጠበት ዋጋ 905,155.50 ሽህ ብር

{12} ጊዳቦ ሆቴል1  የመንግስት ሆቴል በ12/01/95 ዓ/ም፣ ገዢ ወንዶ ገነት ፒኤልሲ የተሸጠበት ዋጋ 505,000 ሽህ ብር

{13} ጊቤ ኢትዩጵያ ሆቴል1  የመንግስት ሆቴል በ9/13/1999 ዓ/ም፣ ገዢ አዲስ ፋና የተሸጠበት ዋጋ 475,999.55 ሽህ ብር

{14} ዋልጋ ኢትዩጵያ ሆቴል@2  የመንግስት ሆቴል በ05/19/99 ዓ/ም፣ ገዢ ወ/ሮ በላይነሽና ሌሎች የተሸጠበት ዋጋ 426,135.39 ሽህ ብር

{15} ወለጋ ኢትዩጵያ ሆቴል4  የመንግስት ሆቴል በ12/01/95 ዓ/ም፣ገዢ አዲስ ፋና የተሸጠበት ዋጋ 517,047.23 ሽህ ብር

{16} ዳህላክ ፓራዳይዝ1  የመንግስት ሆቴል በ07/06/95 ዓ/ም፣ገዢ ወ/ሪ ሬታ ፀሃይ የተሸጠበት ዋጋ 650,000 ሽህ ብር

{17} ቱሪስት ሆቴል1   የመንግስት ሆቴል በ09/29/95 ዓ/ም፣ ገዢ ወ/ሪ አለምፀሃይ ተገኘወርቅ የተሸጠበት ዋጋ 1,100,000 ሚሊዩን ብር

{18} ብሉ ናይል ራስ ሆቴል1 የመንግስት ሆቴል በ07/05/2002 ዓ/ም፣ ገዢ ቤተዛታ ሄልዝ ስርቪስ የተሸጠበት ዋጋ 6,501,100 ሚሊዩን ብር

{19} ወሊሶ ኢትዩጵያ ሆቴል1  የመንግስት ሆቴል በ03/26/2003 ዓ/ም፣ለወ/ሮ ዝምታወርቅ ነጋሽ የተሸጠበት ዋጋ 1,600,000 ሚሊዩን ብር

{20} አምቦ ኢትዩጵያ ሆቴል1 የመንግስት ሆቴል በ4/8/2003 ዓ/ም፣ ገዢ አቶ ታከለ ታደሰ የተሸጠበት ዋጋ 2,623,200 ሚሊዩን ብር

{21} ዋቢሸበሌ ሆቴል ሃዋሳ ቁ15  የመንግስት ሆቴል በ3/4/2005 ዓ/ም፣ለዩናይትድ አፍሪካን ግሩፕ የተሸጠበት ዋጋ 6,950,000 ሚሊዩን ብር

{22} ጋምቤላ ኢትዩጵያ ሆቴል1 የመንግስት ሆቴል በ21/7/2005 ዓ/ም፣ ገዢ ሳውዝ ዌስት ፒኤልሲ የተሸጠበት ዋጋ 3,750,000 ሚሊዩን ብር

{23} ቀEራ ጊዩን ሆቴል (ጎንደር)2  የመንግስት ሆቴል በ6/8/2005 ዓ/ም፣ ለሲጂኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ የተሸጠበት ዋጋ 3,322,000 ሚሊዩን ብር

{24} ሆቴል ዲ አፍሪክ @3  የመንግስት ሆቴል ቀንና ዓ/ም ያልተገለፀ፣ለአቶ ስይፉ ገብረዩሃንስ የተሸጠበት ዋጋ 6,500,000 ሚሊዩን ብር

{25} ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ቁ22  የመንግስት ሆቴል በ24/6/2008 ዓ/ም፣ ገዢ አቶ ኢዬብ ምህረት የተሸጠበት ዋጋ 5,001,919.00 ሚሊዩን ብር

{26} ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ቁ12 የመንግስት ሆቴል በ9/5/2008 ዓ/ም፣ ገዢ አቶ በላይነህ ተስፋዬ የተሸጠበት ዋጋ 11,041,916.40 ሚሊዩን ብር

{27} ሃረር ራስ ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ15/11/02 ዓ/ም፣ ገዢ ወ/ሮ ገነት አበራ የተሸጠበት ዋጋ 11,245,120.75 ሚሊዩን ብር

{28} ጎሃ ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ25/6/2009 ዓ/ም፣ ገዢ ቤታስ ኢንዱስትሪ ፒኤልሲ የተሸጠበት ዋጋ 20,000,116 ሚሊዩን ብር

{29} ጣና ጊዩን ሆቴል የመንግስት ሆቴል በ3/5/2009 ዓ/ም፣ ገዢ ብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል የተሸጠበት ዋጋ 42,000,000 ሚሊዩን ብር

{30} ባሌ ጎባ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ8/7/2009 ዓ/ም፣ለገድብ ኢንጅነሪንግ ፒኤልሲ የተሸጠበት ዋጋ 7,500,000 ሚሊዩን ብር

{31} ላሊበላ ሮሃ ጊዩን2   የመንግስት ሆቴል በ25/9/96 ዓ/ም፣ለአጂካ ትሬዲንግ ኤንድ ትራቨል የተሸጠበት ዋጋ 22,001,000 ሚሊዩን ብር

{32} የሃ ጊዩን ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ8/8/2009 ዓ/ም፣ ገዢ ቢቲ አድቨርት ፒኤልሲ የተሸጠበት ዋጋ 21,000,027 ሚሊዩን ብር

{33} ሮሃ ጊዩን ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ2/11/2010 ዓ/ም፣ ገዢ አያት ሼር ካንፓኒ የተሸጠበት ዋጋ 31,640,799  ሚሊዩን ብር

{34} ናሽናል ሆቴል2  የመንግስት ሆቴል በ29/08/02 ዓ/ም፣ ገዢ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሸጠበት ዋጋ 17,406,880.24 ሚሊዩን ብር

{35} ቦኩ ሳፕ1  የመንግስት ሆቴል በ8/7/1995ዓ/ም፣ ገዢ ዲንሾ ኦሮሚያ የተሸጠበት ዋጋ 210,231ሽህ ብር

{36} ጂማ ኢትዩጵያ ሆቴል@2  የመንግስት ሆቴል በ3/30/2001ዓ/ም፣ለቀኛዝማች ተካ ኢገኖ የተሸጠበት ዋጋ 611,432.40ሽህ ብር

አጠቃላይ የሆቴል ኢንተርፕራይዞች ሽያጭ 246,558,352.70 ሚሊዩን ብር ነበር፡፡

የሽያጩ ዓይነት (Type of sale) 1የቢዝነስ ሽያጭ፣(Business sale)፤2 የንብረት ሽያጭ፣(Sale of  asset)፤3 (አጠቃላይ ሽያጭ ቢዝነሱንና ህንፃውን)፤

4 ቢዝነስ/ኤምኢቢኦ፣ Business / Management/Employee Buyout (MEBO)፤ለማነጅመንትና ለሠራተኛ የተሸጠ ሆቴል 5 Joint venture፤አሽሙር ንግድ

@ These are properties returned to former owners in accordance with Proclamation No. 110/1995. Source: Privatization and Public enterprises supervising agency and own competition.

{1} በፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ለቀድሞ የሆቴል ባለቤቶቻቸው የተመለሱ ሆቴል ዲ አፍሪክ ለአቶ ሰይፉ ገብረዩሃንስ፣ ግሸን ሆቴል ጊዩን ለወ/ሮ ይህደጋ ገብረስላሴ፣ ዋልጋ ኢትዩጵያ ሆቴል ለወ/ሮ በላይነሽ፣ ጂማ ኢትዩጵያ ሆቴል ለቀኛዝማች ተካ ኢገኖ ንብረታቸው ተመልሶል፡፡

{2} የመንግሥት ፓርቲዎች ንብረት Government Party property

የመንግሥት ፓርቲዎች ንብረት ከመንግሥት ሆቴል ኢንተርፕራየዝ ሽያጭ፣ዋንዛዬ ሆቴልን የአማራ ልማት ማህበር፣ ናሽናል ሆቴልን የኢትዩጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን፣ ቦኩ ሳፓ ዲንሾ ኦሮሚያ እንዲሁም በአዲስ ፋና ማናጅመንትና ሠራተኞች የተሸጡ ሆቴሎች፣ ተራራ ሆቴል፣ ራስ ግሪል፣ ጊቤ ኢትዩጵያ ሆቴልና፣ ወለጋ ኢትዩጵያ ሆቴል ይገኙበታል፡፡ የአዲስ ፋና ጀነራል ማርቸንዳይዝ ኤንድ ሆቴልስ ትሬድ ሼር ካንፓኒ፣ የፋይናንስ ማናጀር አቶ አስራትወርቁ ሃይሌ ከሚል መረጃ በስተቀር ስለ አዲስ ፋና ኮንፓኒ ታሪክ፣ሹር ሆልደርስ  ባለቤቶች የሚገልፅ ነገር ሁሉ ድብቅ ነው፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ድርጅት መሆኑ እውን ነው፡፡

{3} ሜድሮክ ኢትዩጵያ  Midroc Ethiopia

የሜድሮክ ኢትዩጵያ ባለቤት ሽህ መሃመድ አላሙዲን ከህወኃት የመንግሥት ሆቴል ኢንተርፕራየዝ ሽያጭ፣ በፕራይቬታይዤሽን ስም ከተቀራመቱት የቅርጫ ድርሻ አንደኛው መስቀል አደባባይ የሚገኘው ራንዴቩ ካፍቴሪያ  በሚስታቸው ወ/ሮ እንይሽ አስረስ  በሁለት ሚሊዩን ስምንት መቶ ሽህ ብር የተሸጠላቸው ንብረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ደብረዘይት የሚገኘው ራስ ሆቴል በስምንት ሚሊዩን ስባት መቶ ሽህ ብር በርካሽ ዋጋ የተቸበቸበው የህዝብ ንብረት ይጠቀሳሉ፡፡

{4} እቴጌ ጣይቱ ሆቴል Taitu Hotel

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ይገኙ የነበሩ ስዕሎች

በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በደርግ አገዛዝ ስርዓት የተወረሱ መንግስታዊ ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘወወር በ1994 ዓ/ም በአዋጅ የተቆቆመ ድርጅት ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ (ስዬ አብርሃ ወንድም) 05/19/99እኤአ ለእህታቸው ባል አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአምስት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሽህ ብር (5,273,000 ) ሸጡላቸው፡፡ በኢትዩጰያ የመጀመሪያ የሆነውን ጥንታዊ ሆቴል የሃገር ሃብትና ቅርስ ሆኖ ሳለ በህወሃት/ኢህአዴግ ታሪክን የማጥፋት የቆየ ደመኝነት ለዘመዳቸው እንዲሸጥ ተደረገ፡፡ ገዥው 35 በመቶ 1,845,550 ብር ከፍለው ቀሪውን 3,427,450 ብር በአምስት አመታት ውስጥ በአመት  685,490 ብር እየከፈሉ ለመጨረስ ተስማምተው ቅርሱን በእጃቸው አስገቡ፡፡ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ጥር 3 ቀን 2007 እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር በ109 አመቱ በእሳት ተቃጠለ፡፡

አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣ በመለስ ዜናዊ ውርስና ቅርስ የሆነው የሙስና ፋብሪካ ምርት አምራች  ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ (ስዬ አብርሃ ወንድም) 05/19/99እኤአ ለእህታቸው ባል አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣ከሸጡላቸው ውስጥ፡-

{1}እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአምስት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሽህ ብር (5,273,000 ) ሸጡላቸው፡፡

{2}የጉለሌ የሳሙና ፋብሪካ በ12/23/1996 አ/ም በ22,370,000 (በሃያ ሁለት ሚሊዩን ሦስት መቶ ሰባ ሽህ ብር) ገዝተዋል፡፡{3}ሐረር ፕሪንቲንግ ኢንተርፕራይዝ ማተሚያ ቤትን በ1,164,000 (አንድ ሚሊዩን አንድ መቶ ስድሳ አራት ብር)  በ10/18/1995 ዓ/ም ገዝተዋል፡፡ በጥናት እንደተረጋገጠው በኢትዮጵያ አይን ያወጣ ሙስና ሌብነት የተጀመረው በመለስ ዜናዊ ፊት አውራሪነት በህወኃት፣ በብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴግ፣ ወዘተ  ዘመን አገዛዝ ሲሆን፣ይህውም  በ1994 ዓ/ም አዋጅ መነሻነት ከመንግሥታዊው ዘርፍ ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘወወር በተቆቆመው ድርጅት ‹‹የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ›› ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ አማካኝነት የህዝብ ሃብት የተሸጠበት ጊዜ ነበር፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን፣የመንግሥት እርሻዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆቴሎች ወዘተ ተሸጡ፣ የከተማ መሬት በሊዝ ስም ተሸጡ፣ የገጠር መሬት ለኢንቨስተሮች ተሸጡ!!! ብሎም የትግራይን ክልል ድንበር ማስፋት ተያያዙት!!! የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለማጣላት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡  በህግ ስም! በአዋጅ  ሰም! ዘረፋ ህጋዊነት እንዲያገኝ ተደረገ፡፡ ዛሬ የምናያቸው ሃብታሞች ትላንት ቁምጣ አድርገው፣ ሸበጥ ተጫምተው፣ ቦንብ ታጥቀው፣ ክላሽ ደግነው በጉልበት ያስገበሩን ወራሪዎች የሃገሩን ኃብት ገና ዘርፍው አልጠገቡም!!! ቪላ ቤት ሰሩ አልጠገቡም፣ ፎቅ ገነቡ አልጠገቡም! ሚሊዮነር ሆኑ አልጠገቡም! መቼም አይጠግቡም፡፡ ስለዚህ ታግሎ ከመንቀል ሌላ መፍትሄ የለም!!! እነዚህን የመንግሥት ሆቴሎች፣ እርሻዎችና፣ ፋብሪካዎች በቀጣይነት እንዘግባለን፡፡ የተደረገውን ዘረፍ የሚያውቁ ሁሉ ለመጻፍ አይስነፉ፣አይፍሩም ለነገው ትውልድ የኃብቱ ምንጭ በዘረፋ የተገኘ መሆኑን ምስክርነታችንን ማቆየት ግድ ይላልና!!!

የኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ኃላቀር በመሆኑ ነፃ የገበያ ውድድር ያለመኖር፣ የመዋለ-ንዋይ ፍሰት ችግር፣ የፋይናንሻል ሃብት እጥረትና የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወተው ሚና ደካማነት ወዘተ ተደማምሮበት የፕራይቬታይዜሽን ሽግግር የተጨናገፈ ለመሆን በቅቶል፡፡ በኢትዩጵያ የፕራይቬታይዜሽን ሽግግርና ሂደት በቂ በሆነ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ባለመሳተፋቸው ምክንያት አብዛኛዎቹ የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ሜድሮክ ካንፓኒዎችና ኢፈርት ድርጅቶች በሙስና፣ በአድሎና በዝምድና አሰራር ንብረቶቹ  ማዘዋወራቸው ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ የፕራይቬታይዜሽን ክንውን የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ያገለለ፣ ያለ ገበያ ውድድር የተቸበቸቡ፣ በመሆኑ ውጤቱም የብዙ ሠራተኞች ቅነሳን ያሰከተለ፣ ምርታማነትን የቀነሰ፣ ተጨማሪ ኢንቨስትመንትን ያልጨመረና፣ የህዝብ ኃብት ለጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሸጡ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡

Addis Ababa’s iconic Taitu Hotel burned to the ground; it took firefighters over 1 hour to arrive even though they were stationed only 5 minutes away. The 108-year old Taitu Hotel was burned beyond repair (sustained 75% damage) while fire fighters stood idly by until it was to late, despite the claim by the government that the fire was controlled quickly

ምንጭ/, Reference

1- JOURNAL OF ECONOMICS AND INTERNATIONAL BUSINESS RESEARCH (JEIBR) ISSN: 2328-4617,VOL. 1(2), pp. 35-54, JULY 2013,REF NUMBER: 0520130801 ONLINE: http://www.projournals.org/JEIBR

2- http://taituhotel.com/.

3- Privatization and Public enterprises supervising agency and own competition.

በፕራይቬታይዜሽን ስም ሚሊየነሮች የሆኑ በኢኮኖሚ መርማሪ ኮሚሲዩን ይመርመሩ!!!

ህወኃት ኢህአዴግ የተዘረፍነውን ኃብት ማስመለስ ታሪካዊ ግዴታ አለብን!!!

የብሄራዊ ዳቦ ድርሻ ጥያቄችን ይመለስ!!!

የፀረ-ሙስና ትግላችን ይቀጥላል!!!

ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት፣ የፖለቲካ ነፃነት የለም!

Share.

About Author

Leave A Reply