እየሱስ ከርስቶስ ለምን አልሸሸም?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ደቀመዝሙርቱ አየሱስ ክርስቶስ እንዲሞት አይፈልጉም ነበር። አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ቶሎ ይሞታል ብለው አስበውም አልመውም አያውቁም ነበር፤ እሞታለሁ እያለ ደጋግሞ ቢተነብይላቸውም። ባለጋራዎቹ እየሱስን ሊይዙ በመጡበት ሌሊት ችኩሉ ደቀመዝሙሩ ጴጥሮስ ከወታደሮቹ የአንዱን ጄሮ በሰይፉ መትቶ ቆረጠው። እየሱስም “ሰይፍህን ወደሰገባው መልስ፤ ሰይፍ የሚመዘዙ በሰይፍ ይጠፋሉ። እኔ ብጸልይ ለእኔ የሚመክቱ ዙ ሺ መላእክት አባቴ አይልክልኝምን?” ሲል ተናገረው። ከዛም የተቆረጠውን በጆሮ አንድቶ ያልተቆረጠው ላይ ሰክቶ ጆሮውን ፈወሰው። እየሱስ እንዲያመልጥ የደቀመዛምርቱ የፍላጎት ቢሆንም እሱ በፍቃደኝነት ለወታደሮቹ እጁን ሰጠ። አራጆቹ ሊያርዱት ሲወስዱት እየተጎተተ እንደሚሄድ በግ ዝም ብሎ ሊሞት ተወሰደላቸው። ግን ለምን እየሱስ ከክርስቶስ ቀደም ብሎ ሊሸሽ ሲችል አልሸሸም?

ምክንያቱ፥ ወደእዚህ ዐለም የመጣው እንደ እኛ ለመኖር ሳይሆን ለመሞት ነበርና። ለምን መሞት ነበረበት? ከ እዛ 5500 ዐመት እስቀድሞ እሞታለሁ ብሎ ቃል ስለገባ።በምን ሁኔታ? መልሱ ወደሁለት ሰዎች አመጸኝነት ይመልሰናል። ሰዎቹ ባልና ሚስት ነበሩ። ብዙዎቻችሁ ስማቸውን ሳትሰሙ አትቀሩም። አዎን — አዳም እና ሄዋን።

የሁለቱን ሰዎች ታሪክ ያነበባችሁ ወይም የሰማችሁት እንደምታውቁት ባልና ከሚስቱ እንደእግዚአብሄር አዋቂ እንሆናለን ብለው አትብሉ የተባሉትን የእውቀት ፍሬዌች ስለበሉ ነው። ሰው ከመፈጠሩ በፊት በሰማይ ክብር የነበረው እና እሱም ፍጡር የሆነው ፈጣሪ እሆናለሁ ብሎ ተዋርዶ ከሰማይ ተባሮ የነበረው ለሳጥናኤል አማልሎ አስበላቸው። መጀመሪያ ሴቲቱን አስበላት። እሷ ደግሞ ባሏን አበላችው። ባልየው እምቢ ለማለት ይችላል ነበር። ከፈጣሪው ይልቅ የሚስቱን ስለአፈቀረና ስለታዘዘ በላ። በእዚህ አኳኋን ባልና ከሚስቱ በአመጸኝነታቸው ከሳጥናኤል እኩል ሆኑ።

ይህ ከእግዚአብሄር በስተጀርባ የተፈጸመው የክህደት ወንጀል በእስራት ሳይሆን በሞት የሚያስቀጣ ከባድ ወንጀል high treason ነበር። እግዘብሄር ችግር ውስጥ ገባ። ሰዎቹን እጅግ ያፈቅራቸው ነበር። እንዳይገላቸው እጅግ ያፈቅራቸልዋ። እንዳይምራቸው ፍርድ ሊገመድል ሆነ። በእዚህ ላይ ሳጥናኤል እኔ ከሀጥያት መሠርቼ ከሰማይ አባረህ ቀጥተኸኝ እነሱም አንተ የከለከልካቸውን አድርገው እንደ እኔ አምጸው እነሱን ልትምራቸው ነውን ሳይለው አልቀረም? ስለዚህ እግዚአብሄር አዘነ። ህግ ተደንግጎ ሰዎቹ በትቢቡትእና አመጻ ህጉን ስለጣሱ ህግን ለማስከበር ሞሜት ፍርድ መፍረድ ነበረበት። ስለእዚህ ለሁለቱ ሰዎች የሚገባውን ሞት ያኔ ቃል ይባል ወደ ነበረው፥ ዛሬ እየሱስ ክርቶስ ወደ እምንለው ወደ ልጁ አስተላለፈው። እየሱስም እንደ አባቱ ሰውን እጅግ ይወድ ስለነበር ከ 5500 ዐመታት በኋላ ሰው ሆኖ ተወልዶ በሁለቱ ሰዎች እና ከእነሱ በደማቸው ውስጥ ሀጥያታቸው በተላለፈባቸው ልጅ ልጆቻቸው ፈንታ ራሱ ሊሞት ፈቀደ። በእነሱ የደም ፈንታ ስለፍቅሩ የራሱን ደም በማፍሰስም የእነሱን የሞት ፍርድ ተሸክሞላቸው ከመንፈሳዊ ሞት አዳናቸው። ይህም ማለት በእግዚአብሄር ላይ ከማመጻቸው በፊት መንፈሳቸውን እና አካላቸውን ሀጥያት ስላልበከለው ህይወታማ እና ንጹህ ነበር። ሀጥያት ባይሠሩ ኖሮ ልጆቻቸ ሄኖክ እና ኤልያስ እንደ አረጉት እነሱም ለብዙ ዘመን ኖረው በመንፈስም በአካልም ሳይሞቱ ያርጉ ነበር።

ሀጥያት ከመሥራታቸውም በፊት ያለእፍረት እና ወንጀለኝነት ሜማት ከእዚዙአብሄር ጋራ ይገኙኘ ነበር። ከአመጻቸው በኋላ በእነሱ እና በእግዚአብሄር መሀል የሀጥያት ግድግዳ ተገነባ። በዚህ ምክንያት ከገነት ተባረው ጥንት ወደተፈጠሩባት ኤልዳ ወደተባለችው ሰፍራ (ኢትዮጵያ ናት ብዬ አስባለሁ) ተወረወሩ። ዘለአለማዊ ህይወትንም አጡ። ከ 5500 ዐመትታ በኋላ ቃሉን ጠብቆ፥ የሰማይ ክብሩን አራግፎ፥ ድሀ ሆኖ በቤተልሄም ኤፍራታ ተወለደ።

እንግዲህ ደቀመዝሙርቱ ሽሽ ሲሉት እና ራሱም ሊሸሽ ሲችል እየሱሰ ክርቶቴስ ያልሸሸው በእሱ በሞት አዳምን እና ሄዋንን እዲሁም ምድሪቱን የሞሉትን የእነሱን ልጆች ሁሉ ሱሰ እንደሞተላቸው ተረድተው ካመኑበት በእግዚአብሄር እና በእነሱ መሀል የተገነባውን የሀጥያት ግድግዳዬ አፍርሶ ከእግዚአብሄር ጋራ አስታርቋቸው ሲሞቱ ደሞ ጥንት አዳም እና ሄዋን ተባረው ወደነበረባት ወደ ገነት መልሶአቸው ለዘላለም ሊያኖራቸው በምህረቱ ፈቅዶ ነው። ለእኔ እንደገባኝ፥ እየሱስ ሊገድሉት ሲሉ ያልሸሸው እና ወዶ ተሰቅሎ የሞተው ስለዚህ ነው።

(ፍቅሬ ቶለሳ ፕሮፌሰር)

Share.

About Author

Leave A Reply