ኦዴፓ ወደ አንባገነንነት ከገባ ከወያኔ ይብሳል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

እዚህ ጋ አንድ አውነት እናስተውል። ማይኖሪቲ ስልጣን ላይ ሲወጣ ከፋፍሎ ለመግዛት የጭቆና ስርአት ቢገነባም፣ የስርአቱ ቅቡልነት በሀይለኛው አሽቆልቁሎ እንዳይጥለው ለታይታ እና የውጭውን አለም ለማሳመኛ ልማትን እንደ አዋጪ መፍትሄ ስለሚያየው በርትቶ ይሰራል።

ኢህአዴግ በመለስ ስር የጭቆና ቀንበሩ ከሰብአዊ ልማት አንፃር የከፋ ቢሆንም ቁሳዊ ልማት ለማስመዝገብ ተፍ ተፍ ብሏል። በቁጥር የበዛ (ማጆሪቲ ላለማለት ነው፣ ኢትዮጵያ በአንድ ብሄር ማጆሪቲ የላትም) ብሄርን የሚወክል ቡድን ሁሉንም አካታች ስርአት ገንብቶ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ካልመራ በስተቀር አንባገነን ቢሆን እንደ ማይኖሪቲ ቡድን የጭቆና ስርአቱን በልማት የማጌጥ እድሉ እንኳ የለውም።

ቅቡልነቱ ያለው በቁጥር መብዛቱ ላይ ስለሆነ በፈጣን ልማት የሰውን ህይወት በመለወጥ አካሄድ ላይ ዳተኛ ይሆናል። የመኖር ወይ የመሞት ሽረት አይነት ትግል በልማት ላይ አያካሂድም።

ሊያደናቅፉት ዘውትር ከሚሹ ማይኖሪቲዎች ጋር ሲባላ ሲናከስ እና የውስጥ ሴራውን በማክሸፍ ስለሚጠመድ አቅዶ፣ እቅድን ለማስፈፀም ጊዜ የለውም። የልማት አጋሮቹም አያምኑትም።

ኦዲፒ አንባገነን ከሆነ ከወያኔ የከፋ ነው የሚሆነው።

(ሙክታር ኡስማን)

Share.

About Author

Leave A Reply