ኦፒዲኦ ለነጋሶ ጊዳዳ በየወሩ ሰላሳ ሺህ ብር ሊከፍላቸው ነው መባሉን አስተባበለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በቅርቡ የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጂት (ኦህዴድ) አንድ ዘመናዊ መኪና ሊገዛላቸውና በየወሩ 30 ሺህ ብር ደሞዝ ሊከፍላቸው ተወስኗል በሚል በተለያዩ ሚዲያዎች የቀረበውን ዘገባ ማስተባበሉ ተነገረ።

የድርጂቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ነጋሶ ጊዳዳ ያሳለፉትን የ13 አመታት የችግር አመታት በመገንዘብ ሊደግፋቸው ወስኗል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙሀን በስፋት መዘገቡ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ዶክተር ነጋሶ ሁኔታውን በሚጠይቁበት ወቅት “ድርጅቱ እንዲህ ያለ ውሳኔ አልስተላለፈም” የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፕሬዚዳንትነት ከወረዱ በኋላ በሀገሪቱ ህግ መሰረት ሊያገኙ የሚገባቸውን ማንኛውንም ጥቅም እንዳያገኙ መደረጉ የሚታወቅ ነው።

ይሁንና የኦሮሚያ ክልል በቅርቡ አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው መዘጋጀቱን የሰሙት ነጋሶ ሁኔታው እጅግ ያስደሰታቸው መሆኑን ቢገልጹም ተስፋ ብቻ ሆኖ መቅረቱ ግን እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል። ~ ቃሊቲ ፕሬስ

 

Share.

About Author

Leave A Reply