ከሻምቡ ወደ ነቀምቴ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከሆሮ ጉዱሩ ዞን ሻምቡ ከተማ ወደ ነቀምቴ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ በሰዎች ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

45 ሰዎች የመጫን አቅም የነበረው ህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ፤ መጫን ከነረበት አቅም በላይ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር አደጋው አንዳጋጠመው የሆሮ ጉዱሩ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ተፈራ እንደተናገሩት፥ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ባሳለፍነው ቅዳሜ ነው ባኮ እና ሀረቶ በሚባሉ አካባቢዎች መካከል ላይ በሚገኝ ለገ ጂማ ስፍራ የተገለጠበው።

በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ላይ በደረሰው አደጋም የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉን ሀላፊው አስታውቀዋል።

በትራፊክ አደጋውም የበህዝብ ማመላለሻው አሽከርካሪ እና ረዳትን ጨምሮ ከተሽከርካሪው ውጨ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል።

በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ በተሽከርካሪው ላይ ተሳፍረው የነበሩ በርካታ ሰዎች ላይ ከቀላል አስከ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ገልፀዋል። እንደ አቶ ደሳለኝ ደለፃ፥ የመገልበጥ አደጋ ያጋጠመው ተሽከርካሪ ለረጀም ዓመት አገልግሎት የሰጠ እና ያረጀ ነው።

FBC

Share.

About Author

Leave A Reply