ከቅርብ ሰአታት በፊት በሶሻል ሚዲያ በተለቀቀ መግለጫ የኢሳት ባልደረቦች የስም ዝርዝርና ፊርማ ይዞ ወጥቶአል ። ከተዘረዘሩት የኢሳት ባልደረቦች ውስጥ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

1. አቶ ኢርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ 2. ወ/ት ሪዮት አለሙ 3. ወ/ት ብርታዊት ግርማይ 4. አቶ ብሩክ ይባስ 5. አቶ ግርማ ደገፋ ቅነሳው እንዳማይመለከታቸው ፣ እነሱን እንደማያካትት ለኢሳት ደጋፊዎችና ለህዝብ ግልጽ ለማድረግ እንወዳለን። ቀድም ሲል በሶሻል ሚዲያ “መረጃ” በሚል የተለቀቀውን መሰረተ ቢስ ሸፍጥ መሆኑ የሚያሳየው የተለየ “የፓለቲካ አቋም” ያላቸው ስማቸው የተዘረዘሩት ግለሰቦች በኢሳት ውስጥ እንዲቀጥሉ አይደረግም ነበር። ቅነሳው ሌሎች በዚህ መግለጫ ውስጥ ስማቸው የሌለና “የፓለቲካ አቋማቸውም” ከእነዚህ ጋር በተቃርኖ የሚገኝ እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ እወዳለሁ።

ከሚያዚያ ወር (April) የኢሳት ዲሲ ደሞዝ የተከፈለው አርቲስት አክቲቪስት ታማኝ በየነ የኢሳት ዲሲ ዋና ዳይሬክተር በዋነኝነት እንዲሁም እኔ በተባባሪነት በጎ ፈቃድ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች $50, 000 ብድር ተወስዶ የተፈጸመ መሆኑን ይፋ ማድረግ እወዳለሁ። ይህን ደግሞ መግለጫውን ያወጡትም ሌሎች የኢሳት ባልደረቦች በሙሉ የሚያውቁት ጉዳይ ነው። ምንም ሚስጥር የሌለው ሃቅ ነው። ባለፈው ወር ግንቦት (May) በትላንናው እለት ደግሞ ለተቀነሱትም ሆነ ለሚቀሩት የተፈጸሙ ክፍያዎች የቦርድ አባላት በገቡበት ከባንክ የተወሰደ ብድር ጭምር የተፈጸመ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ።
በ አፕሪል 18፣ 2019 በኢሳት ቴሌቪዥን በወጣው የስራ አስፈጻሚ ቦርድ መግለጫና እኔም ቦርዱን በመወከል አጭር ማብራሪያ በኢሳት ቴሌቪዥን እንደሰጠሁት፣ ኢሳትን የህዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ፣ እንደ አዲስ ለማወቀር፣ አዲስ ቦርድ የማስምረጥ (በባለድርሻ አካላት በጋዜጠኞችም የተጠቆሙ ጨምሮ) ሂደት ያለው መሆኑን፣ ይህን ሂደት እንደተጀመረም አስታውቀናል ። በዛሬው መግለጫም ይህ ተጠቅሶአል።

ቅነሳው በከፊል የተደረገው በቀዳሚነት(seniority) ሲሆን፣ አንዳንድ የኢሳት ፕሮግራሞች ፣ ሬድዮ ፕሮግራም ጨምሮ ማጠፍ የግድ ስለሆነ ጭምር መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ። ያም ሆኖ ግን ለተቀነሱት ሁሉ የተሰጠው አማራጭ የራሳቸውን ፕሮግራም በማስታወቂያና በስፖንሰሮች እንዲሸፍኑ ለመንቀሳቀስ እንደሚችሉ ነው። ዋናው ኢሳት እንደቀደሙት አመታት ከዚህ በፊት በነበረው መጠነ ሰፊ በጀት ሊቀጥል ፈጽሞ የማችልበት ደረጃ በመድረሱ መሆኑ መታወቅ አለበት። በዚሁ ምክንያት በአውሮፓ በለንደንና በአምስተርዳም የሚገኙ ስቱዲዮችንም በሚመለከት ቦርዱ የበጀትና የቅነሳ እርምጃ በቀጣይነት ይወስዳል።

ነገር ግን አሁን የተቀነሱትም ሆነ ያልተቀነሱት ደብዳቤ ተፈራርሞ ወደ አደባባይ በማውጣት ወደ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚቻልበት ወይንም ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም። በውይይትና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተደማምጠው በሚድረግ ሂደት መሆኑን ለአለፉት ወራት ለማሳሰብ ሞክረናል ። ሌሎች ለቦርዱ በተጻፈ ደብዳቤ ሆነ በመገለጫ ላይ የተካተቱ ነጥቦች፣ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ ጨምሮ ፣ በኦዲተሮች ጭምር ተመርምሮ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ምንም ችግር የሌለበት ጉዳይ መሆኑን፣ ነገር ግን ጥቂት ባልደረቦች አሁን ይደረግ ስላሉ፣ ሱሪ ባንገቴ እንደሚባለው በፈንግጭው ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ሊሆን ይገባል።

አንዳንድ ወገኖች፣ ከዚህም ከዚያም ያልተረዱት ኢሳት አሁንም በርካታ ባለድርሻዎች የሚገኙበት፣ (ማለትም፣ አሁን የሚገኘው ቦርድ፣ አሰተዳደር፣ ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም በአለም ዙሪያ የሚገኙ የድጋፍ ኮሜቴዎች) እንዲሁም ደግሞ እንደማንኛውም ተቋም በህግ የተመዘገበ፣ በፓሊሲ፣ በስርአትና ደምብ፣ በተቋማዊ ሂደት (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም፣ እሳት የማጥፋት አይነት ውጣ ውረዶች) የሚሄድ እንጂ ይህ ወይንም ያ ባለድርሻ አንድ ብቸኛ አካል ወይንም ሌላው ባለድርሻ በአንድ ጉዳይ ካልተስማማ እንደፈለገና እሱ በተመቸው መንገድ ብቻ ሊሄድ እንደማችል መታወቅ አለበት።

ይህን ሃቅ በተደጋጋሚ በግልም በቡድንም ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማስረዳት በርካታ ወራቶች ተቆጥረዋል። በህግ አግባብም ቢሆን ኢሳት የራሱ ጠበቆች ያሉት በመሆኑ፣ ይህን ጉዳይ እኔ ያልኩት ካልተደረገ አፈርሳለሁ የሚለው አካሄድ የህግ የበላይነት ባለበት በአሜሪካን ሀገር እንደማይሰራ መግለጫውን ያወጡት ወገኖች ቢገነዘቡ መልካም ነው።

አሁንም ቢሆን መግለጫውን ያወጡት የኢሳት ባልደረቦች ባለፉት ጥቂት አመታት ለኢሳትም ሆነ ለትግሉ ያበረከቱትን አስተዋጾ እኔም ሆንኩኝ በስራ አስፈጻሚ ውስጥ የሚገኙ ባልደረቦቼ የምናከብር መሆኑን ለነሱም ሆነ ለሁሉም ወገን ለማረጋገጥ እወዳለሁ።

Share.

About Author

Leave A Reply