ከባለቤቱ አንደበት (የኋንስ መኮንን)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

AIzaSyAhh1WmxP-pu3yuICFqUc3B3Z0vYw7ptL0የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው “በኦሮሚያ ክልል ህዝብና መንግስት ላይ የተከፈተው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሊቆም ይገባል” ሲሉ መግለጫ መስጠታቸውን ሰምተናል::

በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ይህ የኦዴፓ መግለጫ ግራ አጋብቷቸዋል:: ግርታው የተፈጠረው “ኦዴፓንም ሆነ የኦሮሞን ህዝብ ስም በማጥፋት የተከሰሰው ማን ነው? መልእክቱ እንዲደርስ የተፈለገው ለማን ነው?” የሚል ነው::

ዛሬ ምሽት የጃዋርን OMN ቲቪ ስመለከት አቶ ጃዋር ቃለ ምልልስ እየሰጠ ነበር:: ውይይቱ የተካሄደው በኦሮምኛ ቋንቋ ሲሆን ዋንኛው ማጠንጠኛው “ኦዴፓ” እና ወቅታዊ “መግለጫው” ነበር::

ቃለመጠይቅ አቅራቢው አቶ ተስፋዬ “ኦዴፓ የፓርቲዬ እና ኦሮሞ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብናል” ያለው አንተን አፍህን ለማዘጋት ነው እያሉ ነው:: አንተ ምን ትላለህ?” ሲል ጃዋርን ጠይቆታል:: ጃዋር እንዲህ ሲል መልሷል::

ኦዴፓን ከሞት ያነሳሁት እና ስሙን ያደስኩለት እኔ ነኝ:: ከእኔ ጋር (ኦዴፓ) እንዲህ ዓይነት ሳፋጣ ቢያቆሙ ይሻላቸዋል። ኦዴፓን እያዳከሙ ያሉት በውስጡ የተሰገሰጉ የድሮው ኦህዴድ ሌቦች ናቸው።

ገላን ላይ 500 ሄክታር መሬት የሸጡ ሌቦች እሁንም ኦዴፓ ውስጥ በሥልጣን ላይ አሉ። ሰበታ ላይ በሌለ ድርጅት ስም 40 ሄክታር መሬት የሸጡ ሌቦች አሁንም በኦዴፓ ሥልጣን ላይ ናቸው።

ወለጋ ላይ ኦነግ ባንኮች ሲዘርፍ አብረው ያዘረፉ እና የተካፈሉ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት አሉ። ወለጋ ላይ የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ካምፕ እንዳይገቡ የሚያደርጉት የኦዴፓ ሰዎች ናቸው:: ምክንያቱም ባንክ ዘርፈው መካፈላቸው ምስጢር እንዳያወጡባቸው ነው። ታከለ ላይ የሚነዛው ጥላቻ ምንጩ ከኦዴፓ ከእራሱ ውስጥ ካሉ ሌቦች ነው። የለማ እና የዐብይ ሥርዓት እየፈራረሰ ነው። የኦሮሚያ መንግሥት በሙሰኞች እና በሌቦች ሽባ (paralyzed) ሆኗል።

ምን ለማለት ፈልጌ ነው? ይህንን ያሉት ሌሎች ጸሐፊዎች ቢሆኑ ኖሮ አቡዋራው ይጬስ ነበር:: ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ ውስጥ አዋቂዎች እንዲህ ዝርዝሩን ሲነግሩን የመግለጫዎቹ አድራሻ ይገለጥልናል:: እነማን “በሾርኔ” እየተነጋገሩ እንደሆነም ይገባናል። በመጨረሻም እንዲህ ብለን ብንሰናበትስ?

1. ኦዴፓ ሆይ ሁሉንም ችግር የተባረረችው ህወሓት ላይ ከማላከክ ራስን ከሌቦች እና ጽንፈኞች የማጥራት ዘመቻ ቢጀመር! 2. እንደተባለው ስምህን የሚያጠለሹት ሌቦቹ ከሆኑ በመግለጫ ጋጋታ ግራ ከምታጋባን ለእነርሱ መላ ፈልግላቸው እና ፊትህን ወደተጣለብህ ሀገራዊ አጀንዳ መልስ! 3. ለመፍታት የቸገረ ህመም ነገርም ከገጠመህ ንገረን እና መድኃኒትህን በጋራ እንፈልግ!

Share.

About Author

Leave A Reply