ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ በተጭበረበረ ቼክ 14 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ሊያወጣ ሲል ተያዘ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ በተጭበረበረ ቼክ 14 ሚሊየን 724 ሺህ ብር ሊያወጣ ሲል ተያዘ።

ተጠርጣሪው አቶ ገመቹ ጫላ በሚል ስም በባንኩ ቅርንጫፍ ባለፈው አርብ የባንክ ሂሳብ የከፈተ ነው።

ዛሬም ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በማምራት በተጭበረበረ የአምበሳ አውቶብስ ቼክ 14 ሚሊየን ብር 724 ሺህ በማውጣት አርብ እለት ወደ ከፈተው የባንክ ሂሳብ ለማዛወር ሲል ነው በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ተደርጎበት መያዙን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

ተጠርጣሪው በሰዓቱ ለባንኩ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊ 1 ሚሊየን ብር ጉርሻ በማቅረብ እንዲፈፀምለት ለማግባባት ሞክሮም እንደነበር ተመልክቷል። FBC

Share.

About Author

Leave A Reply