ከጂማ ቦንጋ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ መንገደኞች መቸገራቸውን ገለጹ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ላለፉት ሁለት ቀናት በተቃውሞ ሳቢያ የተዘጋው የጂማ ቦንጋ መንገድ አሁንም እንዳልተከፈተና መንገደኞች እየተጉላሉ መሆኑን ገልጹ።

የከፋ ዞን አስተዳደር በቡና የመነሻነት ታሪክ ሳቢያ ከጂማ ዞን ጋር እሰጣ ገባ በመግባቱ ነው መንገዱ የተዘጋው።

ለተቃውሞው መነሻ የሆነው የቡናና ሻይ ልማት ሚኒስቴር ከዞኑ ጋር ሊያደርገው የነበረውን አመታዊ የቡና ቱሪዝም በአል በመሰረዝ ከጅማ ዞን ጋር ለማድረግ መወሰኑ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንኑ ሁኔታ የተቃወሙ የዞኑ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ላለፉት ሁለት ቀናት ከፍተኛ ተቃውሞ በማድረግ መንገዶችን መዝጋታቸው ይታወቃል።

ይሁንና በዚህ በኩል መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ የወሰደው እርምጃ ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም።

Share.

About Author

Leave A Reply