ከፕ/ር ብርሀኑ ጋር ስንከራከር ቋንቋ አልተቸገርኩም፤ ምክኒያቱም ሰውዬው ትግርኛ አቀላጥፈው ነው የሚናገሩት – አብረሀ ደስታ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ቆይታዬ!
(አብረሀ ደስታ)

ከ5 ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታ በኋላ መቀለ ገብቻለሁ። በቆይታዬ ከብዙ የውጭ ሀገር ኤምባሲ ሰዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ወዳጆች ጋር ተገናኝቻለሁ። በትግራይ ህዝብ ደሕንነት፣ በህዝቦች መቀራረብና በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ እንዲሁም በምርጫ ዝግጅት ዙርያ ተወያይቻለሁ።

አግኝቼ ካነጋገርኳቸው የፖለቲካ መሪዎች የተወሰኑ ኦቦ በቀለ ገርባ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ አይተ ገብሩ አስራት፣ ኦቦ ሌንጮ ለታ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ዶር መረራ ጉዲና፣ ዶር አረጋዊ በርሀ፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ኦቦ ዳውድ ኢብሳ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ (ገለልተኛ ብትሆንም)፣ ዶር ዐብይ አሕመድ … ወዘተ ይገኙባቸዋል።

ከህወሓቱ ተወካይ አይተ ሚልዮን፣ ከአብን ተወካይ አቶ ክርስትያን፣ ከአዴፓ ተወካይ አቶ ብናልፍ አንዷለም እና ከኦዴፓው ኦቦ ለማ መገርሳም ብዙ ባንነጋገርም ተገናኝተን ባውራት እንዳለብን መግባባት ላይ ደርሰናል።

ከሁሉም ጋር የነበረኝ ውይይት ከሞላ ጎደል ጥሩ ነበር። ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ያደረኩት ውይይት ክርክርም ጭምር ነበር። ለሰዓታት ያህል ግዜ ወስደን በ”ኢትዮጵያ ህልውና” ጉዳይ ተከራክረናል። ክርክሩ ጥሩ ነበር፤ ቋንቋም አልተቸገርኩም። ምክንያቱም በትግርኛ ነበር የተከራከርነው!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከኔ በላይ ትግርኛ ቋንቋ አቀላጥፎ ይናገራል፤ ትግርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋው ይመስላል።

ሁላችን የፖለቲካ ፓርቲ ሊቃነ መናብርት ከዶር ዐብይ አሕመድ ጋር በቤተመንግስት ባደረግነው ውይይት መሰረት በሰላምና መረጋጋት፣ ህዝቦች ማቀራረብ፣ ፍትሓዊ ነፃና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ መስራት እንዳለብን ተስማምተናል።

ሰላም ይሰፍን ዘንድ ምኞቴ ነው። አሜን!

It is so!!!

(አብረሀ ደስታ)

Share.

About Author

Leave A Reply