ከ100 በላይ አመራሮች ከሃላፊነት ተነስተዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በታራሚዎች ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን ችግር ለማስቀረት ቀደም ሲል በየማረሚያ ቤቶች የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ አመራሮችን ከሃላፊነት ማንሳቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተናገረ።

አስተዳደሩ እንደተናገረው በፍትህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ #የመብት_ጥሰቶች ሲፈፀሙ ቆይተዋል፡፡ ከነዚህም ተቋማት ውስጥ ማረሚያ ቤቶች እንደሚገኙበትና ይህንንም ለማስተካከል በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው ሲነገሩ እንደተሰማው በየማረሚያ ቤቶቹ ላይ ከዚህ ቀደም ሲፈፀም እንደነበረው የመብት ጥሰት እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዳይኖር ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡ አሁን ላይም ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከዚህ ቀደም የነበረው ችግር አለመኖሩን ባደረግነው ክትትል አረጋግጠናል ብለዋል። ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥም የዳሰሳ ጥናት መደረጉንና ይህም ራሳቸውን ታራሚዎች፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች ወገኖች የተሳተፉበት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ዋነኛ የለውጥ ስራ ለማድረግም በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ሀላፊዎችን በአዲስ እንዲተኩ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በማረሚያ ቤቶች ያለውን የታራሚዎች አያያዝ ይበልጥ ለማሻሻልም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የሚገኙ አራት ማረሚያ ቤቶች በአዲስ እየተገነቡ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገነባው ማረሚያ ቤት ግንባታው 96 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን በዚህ አመት ስራ ይጀምራል ተብሏል። በዚህ አመት ከየማረሚያ ቤቶቹ ከ6 ሺ በላይ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ተደርጓል መባሉን ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሸገር ራዲዮ

Share.

About Author

Leave A Reply