ኩላሊታችንን የሚጎዱ ምክንያቶች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

1 ሽንትን ረጅም ጊዜ ይዞ መቆየት ሽንት በሚይዘን ጊዜ ወዲያዉኑ ማስወገድ (መሽናት) ካልቻልን በፍኛችን ዉስጥ የሚቆየው ፈሳሽ (ሽንት) መጠን እየበዛ ይሄድና በሽንት ቱቦ አማካኝነት ወደ ኩላሊታችን ይመለስና መርዛማ ንጥረ ነገሮች እንዲዘቅጡ ይሆንና የኩላሊት ኢንፌክሽን ይፈጠራል፡፡

2. ጨዉን አብዝቶ መመገብ በምንመገበው ምግብ ዉስጥ የሚኖረውን የጨው መጠን መመጠን (ማሳነስ ) ካልተቻለ ለኩላሊት ህመም ሊያጋልጠን እንደሚችል አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

3. ስጋ አዘውትሮ መመገብ  በምንመገበው ስጋ ውስጥ ፕሮቲን በብዛት ይገኛል ይህን ፕሮቲን የመፍጨት ሂደት ደግሞ ammonia የተባለውን ለኩላሊት ጠንቅ የሆነ ንጥረ ነገር በብዛት ይመረታል፡፡

4. አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን በብዛት መጠቀም ካፌይን የበዛባቸውን አነቃቂ ነገሮችን መጠቀም የልብ ምትንና የደም ዝውውርን ስለሚጨምር በኩላሊታችን ላይ የሚኖረውን ጫና ጨምሮ ለጉዳት ይዳርገዋል፡፡

5. ዉሀ በብዛት አለመጠጣት  ዉሀ በብዛት የማንጠጣ ከሆነ በደማችን ውስጥ የሚኖረውን መርዛማ ንጥረ ነገሮች ክምችት (concentration) ስለሚጨምር ኩላሊታችን ላይ የሚኖረውን ጫና ይጨምረዋል፡፡ስለዚህ በቀን ቢያንስ 10 ብርጭቆ ዉሀ መጠጣት ከጉዳት
ሊታደገን ይችላል፡፡

6. ወደ ህክምና ተቋም በጊዜ አለመሄድ በዘልማድ ምንም አይነት ህመም ሲሰማን ወደ ህክምና ተቋም የመሄድ ለምዳችን አናሳ ስለሆነ በቀላሉ ሊድኑ የሚችሉ ህመሞች በጊዜው ህክምና ባለማግኘታቸው ተባብሰውና ተወሳስበው ለጉዳት ሊዳርጉን ይችላሉ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Share.

About Author

Leave A Reply