Thursday, January 17

ኩራትሽ ቀን አስጥሎ፤ አየን አራት ኪሎ (ዳን አድማሱ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አራት ኪሎ ~> የአዲሱን አመት መምጣት በጉጉት እየጠበኩ ከጳጉሜ ዝናብ ጋር ሆኜ እስከ አዲሱ አመት መባቻ ድረሰ ከራሴ ጋር እያወራሁ ያደመጥሁት ሙዚቃ ነው። የሆነ እልህ፣ ቁጭት፣ መብሰክሰክ …የሚቀሰቅስ አይነት ሙዚቃ…. አራት ኪሎ!

ዳን አድማሱ ከሀዲ፣ ግፈኛ፣ ውሸታምና አስመሳይ የሆነችውን አራት ኪሎ ነው በግጥሙ የሚጎነታትላት!…… (አራት ኪሎ የንግስናዋ ቤት) ከላዩ ቁጭ ብላ የምትወሸክተውን አራት ኪሎ፣ ያለኔ ማንም የለም ብላ በትዕቢቷ መብትና ፍላጎቱን የደፈጠጠችውን አራት ኪሎ ነው እያነሳ የሚጥላት……በክረምቱ ዝናብ ጭቃ ውስጥ እየቧቸረ በፈራረሰው መንደሯ ውስጥ እየተመላለሰ፣ ያቺ ትዕቢተኛ አሁን ሰክና ሲያገኛት በቆሻሻ ክምሯ ውስጥ ያሉ ልጆቿ ጋር ዳንኪራ እየመታ የሚሳለቅባት….።

“እኔ የአርበኛ ልጅ ነኝ” እያለ ማንነቱን እየነገራት ደግሞ ምን ያህል እንደገፋቺው፣ እንደናቀችው በቁጭት ይነግራታል።

አራት ኪሎ!

ባለፉት 27 አመታት ውስጥ ልማት አመጣሁ ተብሎ ጥፋት ከተሰራባቸው ነገሮች ዋነኛ ማሳያ!…..እንደ ሸረሪት ድር በማህበራዊ ትስስር የተወሳሰበውን ህዝብ፣ እዝያ ቦታ የታሪክ ዳራ የሰበሰበውን ህዝብ፣ ከጎኑ ቤተመንግስት እያየ፣ ከአጠገቡ ጮማ የሚቆረጥበት ጠጅ የሚደፋበት ቤተ መንግስት እየተመለከተ በድህነት ውስጥ ሆኖ እየታዘዘ የኖረውን ህዝብ በልማት ስም የበተነ ስርአት፣ በጎረቤቶቻቸው የሚደገፉ አዛዉንቶችን ከከተማ ውጪ በተቀለሰ ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ አንጠልጥሎ ህይወትን በቤት የለካና ኑሮን ያቃወሰ ልማት……ልማታዊ ጥፋት!!

ሙዚቀኛው የፈራረሰችውን አራት ኪሎ እየዞረ በግሩ ይደመድማታል! በእልህ ይረጋግጣታል!…
በድንገት መጥታ ላዩ ላይ የተሾመችውን ቀዳማዊት እመቤት ምን ያህል ለእሱ ስነልቦና ሩቅ እንደነበረች ይገልጽላታል….እንዲህ እያለ..

ናስማስርሽ
መውዜር ዝናርሽ
ፍቅር አልገዛ
ወርቁ ዲናርሽ
ኪዳን ገድል
ባሓታም አልተማርሽ
የካኽኑን
ደውል አልሰማሽ

ቆሞ የሚጠብቅ ምንም ነገር የለም። ሰውም ጊዜን ማቆም ወይም ማፍጠን አይችልም።..ሙዚቀኛውም በግዑዙና በማይንቀሳቀሰው የፓርላማ ሰአት ላይ ተንጠላጥሎ ፍትህ እና እውነት የሚገኙት በቆጣሪው ሰአት ላይ ሳይሆን በጊዜ መሆኑን ይነግራታል..

የፓርላማው ሰዓት ባይዞርም ደቂቃው
ቀን ሲቆጥር ክሶኝ ጊዜ ሆነን ዳኛው

ግን ደግሞ

“አኔም አልፈልግ አንቺም ሄደሻል

ሁሉም አበቃ ተለያይተናል

እንዲህ ሊያሳየኝ ቀን አንቺን ጥሎ

ስንቱን አሳየኝ ወይ አራት ኪሎ…

እያለ ይሳለቅባታል።……. ተምርያለሁ አዋቂ ነኝ ማለቷንም በሰውነት ሚዛን አስቀምጦ እንዲህ ይመዝናታል…

የፍቅር አዋቂ ካላነሰ ወዶ

ምን ያደርጋል ፊደል ያኩፋዳ ባዶ

ይህንን ሁሉ ስታደርግ ደግሞ በባዶነት በመሀይምነትና በተሰረቀ ባዶ እውቀት እንጂ እውነት በእውቀት በልጣ ተገኝታ አለመሆኑን ያስረዳታል! ሳታውቂ ያወቅሽ ይላታል። እንዲህ እያለ…

የአውራ ዶሮ ቁንጮ ስሙ ነው ኮኮን

ስንቱ ቆቡን ጫነ ያልተማረውን

በማለት ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ተብለው የተኮለኮሉትን ዘመነኛ ምሁራንን በሙሉ ይወርፋል…

እንዲህም እንዲያም ሆኖ ለጥፋቷ በአቡን ወይም በሀይማኖት መሪ እንዳያስገዝታት የራሷ አቡንና የሀይማኖት መሪ እንዳላት ያስብና ደግሞ እየተቆጨ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ይራገማል። አቢዮታዊ ዴሞክራሲ ባለ አቡን፣ ባለ ሼሁን ያነሳል…..

በቄስ ሰፈር ካህን እንዳናስገዝትሽ

ለካስ መቼ ጠፋ አበሜኔት ቤትሽ እያለ መንግስታዊ ሀይማኖቷን ይገልጥባታል…..

…አራት ኪሎ (ቤተ መንግስቱንና መንግስቱን እያለ ነው) ያልፈጸመችው ግፍ የለም……ያውም አፍንጫዋ ስር ላሉ፣ ለሚወዷት፣ ለሚታዘዝዋት፣ ድህነትን ችላ ብለው ከግርጌዋ መኖራቸው ብቻ የሚያኮራቸውን ህዝቦች ተጠይፋ ምን ያህል እንዳጎሳቆለቻቸው እንደ ከዳቻቸው ይህ ሙዚቃ እውነት እውነቱን እያነሳ በስሜት ያስጨፍረናል…….

ይሁንና ግን አራት ኪሎ የበደለችውን ያህል ክፉ አይመኝላትም….

አልበጀሽ ሰላሳው ያተረፍሺው ዲናር

በአቢይ ጾም ያዢና ነፍስሽ ፍቅርን ይማር

እያለ ፍትሀዊ ፍርድና ፍቅርን ይበይንላታል……

“አራት ኪሎ” የተሰኘው የዳን አድማሱ ሙዚቃ በእውነትም እውነት ገላጭና ሊደመጥ የሚገባው ሙዚቃ ነው!

(የትነበርክ ታደለ)የአዲሱን አመት መምጣት በጉጉት እየጠበኩ ከጳጉሜ ዝናብ ጋር ሆኜ እስከ አዲሱ አመት መግቢያ ድረሰ ከራሴ ጋር እያወራሁ ታደመጥሁት ሙዚቃ ነው። የሆነ እልህ፣ ቁጭት፣ ቁጣ…የሚቀሰቅስ አይነት ሙዚቃ….አራት ኪሎ!

ዳን አድማሱ ከሀዲ፣ ግፈኛ፣ ውሸታምና አስመሳይ የሆነችውን አራት ኪሎ ነው በግጥሙ የሚጎነታትላት!…… (አራት ኪሎ የንግስናዋ ቤት) ከላዩ ቁጭ ብላ የምትወሸክተውን አራት ኪሎ፣ ያለኔ ማንም የለም ብላ በትዕቢቷ መብትና ፍላጎቱን የደፈጠጠችውን አራት ኪሎ ነው እያነሳ የሚጥላት……በክረምቱ ዝናብ ጭቃ ውስጥ እየቧቸረ በፈራረሰው መንደሯ ውስጥ እየተመላለሰ፣ ያቺ ትዕቢተኛ አሁን ሰክና ሲያገኛት በቆሻሻ ክምሯ ውስጥ ያሉ ልጆቿ ጋር ዳንኪራ እየመታ የሚሳለቅባት….።

“እኔ የአርበኛ ልጅ ነኝ” እያለ ማንነቱን እየነገራት ደግሞ ምን ያህል እንደገፋቺው፣ እንደናቀችው በቁጭት ይነግራታል።

አራት ኪሎ!

ባለፉት 27 አመታት ውስጥ ልማት አመጣሁ ተብሎ ጥፋት ከተሰራባቸው ነገሮች ዋነኛ ማሳያ!…..እንደ ሸረሪት ድር በማህበራዊ ትስስር የተወሳሰበውን ህዝብ፣ እዝያ ቦታ የታሪክ ዳራ የሰበሰበውን ህዝብ፣ ከጎኑ ቤተመንግስት እያየ፣ ከአጠገቡ ጮማ የሚቆረጥበት ጠጅ የሚደፋበት ቤተ መንግስት እየተመለከተ በድህነት ውስጥ ሆኖ እየታዘዘ የኖረውን ህዝብ በልማት ስም የበተነ ስርአት፣ በጎረቤቶቻቸው የሚደገፉ አዛዉንቶችን ከከተማ ውጪ በተቀለሰ ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ አንጠልጥሎ ህይወትን በቤት የለካና ኑሮን ያቃወሰ ልማት……ልማታዊ ጥፋት!!

ሙዚቀኛው የፈራረሰችውን አራት ኪሎ እየዞረ በግሩ ይደመድማታል! በእልህ ይረጋግጣታል!

ግን ደግሞ

“አኔም አልፈልግ አንቺም ሄደሻል

ሁሉም አበቃ ተለያይተናል

እንዲህ ሊያሳየኝ ቀን አንቺን ጥሎ

ስንቱን አሳየኝ ወይ አራት ኪሎ…

እያለ ይሳለቅባታል።……. ተምርያለሁ አዋቂ ነኝ ማለቷንም በሰውነት ሚዛን አስቀምጦ እንዲህ ይመዝናታል…

የፍቅር አዋቂ ካላነሰ ወዶ

ምን ያደርጋል ፊደል ያኩፋዳ ባዶ

ይህንን ሁሉ ስታደርግ ደግሞ በባዶነት በመሀይምነትና በተሰረቀ ባዶ እውቀት እንጂ እውነት በእውቀት በልጣ ተገኝታ አለመሆኑን ያስረዳታል! ሳታውቂ ያወቅሽ ይላታል። እንዲህ እያለ…

የአውራ ዶሮ ቁንጮ ስሙ ነው ኮኮን

ስንቱ ቆቡን ጫነ ያልተማረውን

በማለት ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ተብለው የተኮለኮሉትን ዘመነኛ ምሁራንን በሙሉ ይወርፋል…

እንዲህም እንዲያም ሆኖ ለጥፋቷ በአቡን ወይም በሀይማኖት መሪ እንዳያስገዝታት የራሷ አቡንና የሀይማኖት መሪ እንዳላት ያስብና ደግሞ እየተቆጨ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ይራገማል። አቢዮታዊ ዴሞክራሲ ባለ አቡን፣ ባለ ሼሁን ያነሳል…..

በቄስ ሰፈር ካህን እንዳናስገዝትሽ

ለካስ መቼ ጠፋ አበሜኔት ቤትሽ እያለ መንግስታዊ ሀይማኖቷን ይገልጥባታል…..

…አራት ኪሎ (ቤተ መንግስቱንና መንግስቱን እያለ ነው) ያልፈጸመችው ግፍ የለም……ያውም አፍንጫዋ ስር ላሉ፣ ለሚወዷት፣ ለሚታዘዝዋት፣ ድህነትን ችላ ብለው ከግርጌዋ መኖራቸው ብቻ የሚያኮራቸውን ህዝቦች ተጠይፋ ምን ያህል እንዳጎሳቆለቻቸው እንደ ከዳቻቸው ይህ ሙዚቃ እውነት እውነቱን እያነሳ በስሜት ያስጨፍረናል…….

ይሁንና ግን አራት ኪሎ የበደለችውን ያህል ክፉ አይመኝላትም….

አልበጀሽ ሰላሳው ያተረፍሺው ዲናር

በአቢይ ጾም ያዢና ነፍስሽ ፍቅርን ይማር

እያለ ፍትሀዊ ፍርድና ፍቅርን ይበይንላታል……

“አራት ኪሎ” የተሰኘው የዳን አድማሱ ሙዚቃ በእውነትም እውነት ገላጭና ሊደመጥ የሚገባው ሙዚቃ ነው!

(የትነበርክ ታደለ)

Share.

About Author

Leave A Reply