ኩዌት በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኩዌት በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታወቀች።

የኩዌት የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ሃገሪቱ ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ ላለመቅጠር ጥላው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታውቋል።

እገዳው የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ተደጋጋሚ ውይይት ካደረጉ በኋላ መነሳቱን፥ የኩዌት ረዳት የሃገር ውስጥ ሚኒስትርና የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ተናግረዋል።

የኩዌት መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ጥበቃ እንዲያደርግም ተስማምተዋል ነው የተባለው።

በኩዌት መንግስት በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ የተጣለው እገዳ አንድ አመት መቆየቱን የኩዌት ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመላክታል።

ከሳምንት በፊት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ወደ ኩዌት ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጓዙ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያውያኑ ሃገሪቱ ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ የተከለከሉ ባዕድ ነገሮችና ቁሳቁሶችን ይዘው በመግባታቸው ለእስርና ለእንግልት መዳረጋቸውን ተከትሎ ነበር ማሳሰቢያውን የሰጠው።

ተጓዦቹ ሃገር ውስጥ ያሉ ወገኖቻቸው ለሌላ ዘመድ አዝማዶቻቸው ወደ ኩዌት እንዲያደርሱላቸው የሚፈልጓቸው ቁሳቁሶችን ይዘው መገኘታቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ የተወቀጠ ጫት፣ ቡና፤ ቆጮ፤ ማር እና ሌሎችንም በመደበቅ ወደ ኩዌት እንዲያሻግሩላቸው በሚፈልጉ ዜጎች ሳቢያ ችግር ይገጥማቸዋልም ነው ያለው።

በዚህ ሳቢያ እቃውን ተቀብለው ለማሻገር በመሞከራቸውም 39 ኢትዮጵያውያን ለእስር መዳረጋቸውን ገልጾ ነበር።

በኩዌት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም ዜጎች ለዚህ ተግባር ተባባሪ የሆኑት ባለማወቅና በስሕተት መሆኑን ለማስረዳት ጥረት እያደረገ መሆኑን ተገልጿል። ~ ፋና

Share.

About Author

Leave A Reply