ኬኒያ ለ44 ሰዎች ሞት ምክኒያት የሆነው ግድብ ባለ ቤቶችን ልትቀጣ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ካለፈው ወር ጀምሮ በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች በመጣል ላይ ያለው ከፍተኛ ዝናብ በአንድ በርካታ ዜጎቿን ገድሎባታል፣ ንብረት አውድሟል፣ ከ3 ሺህ በላህ ሰዎችም አፈናቅሏል።

በመጋቢት ወር ብቻ ከ200 ሰዎች በላይ በጎርፍ ተወስደዋል።

ከሶስት ቀናት በፊት ደግሞ አንድ በግለሰቦች የተገነባ ግድብ ተደርምሶ 44 ያህል ሰዎችን ሲገድል በሺህ የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎችን አፈናቅሏል።

መንግስት የግድቡን ባለቤቶች ለህግ እንደሚያቀርብና እንደሚቀጣ አሳውቋል።

“የዝናቡን መጠን እየተመለከቱ አስቀድመው ውሀውን መልቀቅ ሲኖርባቸው በቸልታ ተመልክተዋል” በማለት ነው የከሰሳቸው።  ~ ቃሊቲ ፕሬስ

Share.

About Author

Leave A Reply