ወንጀል ነክ መረጃ – የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቴሌሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 አንቀጽ 9/1/ሀ እና /ለ/ ስር እና በኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ክስ የተመሰረተባቸው።

የወንጀሉ የአፈጻጸም ሁኔታ እንደሚያስረዳው ፡-

1ኛ.ተከሳሽ መሀመድ አብዱሰላም ጀብሮ፣

2ኛ. ተከሳሽ ማህዲ እስማኤል አደም ሲሆኑ ተከሳሾች የቴልኮም መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት፣ ለመጠቀም እና የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ህዳር 26ቀን 2008 እስከ መጋባት 24 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ሸንኮር ወረዳ ቀበሌ 09 የቤት ቁጥር አዲስ በሆነው መኖሪያ ቤት አንድ ክፍል በመከራየት ጌትዋይ በሚባል የቴሌኮም መሳሪያ አማካኝነት ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ኢትዮ-ቴሌኮም በዘረጋው የቴሌኮም መሰረት ልማት (ኔትወርክ) ሳይሆን በመሳሪያዎቹ አማካኝነት በተዘረጉ ኔትወርክ በኩል እንዲያልፍ በማድረግ ከመሳሪያዎቹ በተገኘው መረጃ መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የተደረጉ 244,224 ( ሁለት መቶ አርባ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሀያ አራት ) ደቂቃ ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን በማስተላለፍ የስልክ ጥሪዎቹ በኢትዮ- ቴሌኮም ኔትወርክ በኩል አልፈው ቢሆን ኑሮ ኢትዮ-ቴሌኮም ያገኝ የነበረውን 1,011,563/ አንድ ሚሊዮን አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሶስት /ብር ወይም በወቅቱ በነበረው የምንዛሬ ተመን ሲሰላ 46,402( አርባ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሁለት ) ዶላር እንዲያጣ ያደረጉ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት/ኢትዮ-ቴሌኮም/ የዘረጋውን ኔትወርክ ወደጎን በመተው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ወንጀል በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የልደታ የወንጀልና ፍታብሄር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀል ዳይሬክቶሬት የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

የክሱን ሂደት ምርመራ እና ክትትል ሲያገናዝብ የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም የፌደራል ዐቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ወንጀሉ በስምምነት የተፈጸመ በመሆኑ እንደ ቅጣት ማክበጃነት እንዲያዝ የጠየቀ ሲሆን ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ አለመኖሩ እንደ ቅጣት ማቅለያነት ተይዞ ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸው በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ15000 (በአስራ አምስት ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጮ ተወስኖባቸዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply