ወንጀሎችን ሁሉ ወደ ጾታዊ ጥቃት ማላከክ ጾታዊ አክራሪነት ነው። (ቤቲ ታፈሰ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

እዚህ አገር አንድ ሰሞን ሴት ላይ አሲድ ይደፋ ኡኡ ይባላል መልሶ ይረሳል ተቋሙ ቀጣዮን የቤት ስራ እየጎለተ የማንቂያ ደውሉን እያየ ሙዳ ስጋ እንዳነቀው አባ ወራ አፍጥጦ ብቻ ቁጭ ብሏል ወይ ጠንከር ብሎ ህጉን አያስቀይር እንዲሁ በራሳቸው አለም ተቆልለው መሞታቸው ነው ይሄን ማህበር ነጥቆ ለደጋግና ወጣት በቂም ላልወረዙ ሴቶች ሰጥቶ በደሎችን መቀነስ ይቻላል……

አንዳንዶቹ ዜናዎች ሆነ ብለው ወንጀልን ወደ ጾታዊ ጥቃት የሚያላክኩት አመጽን ጥላቻን ለማምጣት ነው። ስንት ወንዶች አምሽተው ሲገቡ ለስማርት ፎናቸው ተብሎ ብቻ ተገድለዋል።

አክራሪነት ወደእዚህች አገር ከመግባቱ ሃይማኖትና ቤተሰብን ከመበረዙ በፊት ሃይ ባይ ያስፈልጋል ። ወንጀለኞች ይቀጡ ሴቷን ማስተማር የራሷ የሴቷም ጉዳይ ነው። ልጇን አስተምራ ሌላውን መንግስት ይደጉም ማለት ደሃ አገር ላይ አይሰራም። የማነቃቂያ ፕሮግራሞችና ድጋፎችን በገጠር ላሉት ማድረግ የሁሉም ፋንታ ነው።

….ከዚያ በተረፈ ሴታውያኑ በጀታቸውን ምን እየፈየዱበት እንደሆነና አምጥተዋል የሚባለው ለውጥ ተተንትኖ ተበርብሮ መታየት አለበት በገፍ የሚገባው እርዳታ ስንት ፐርሰንት ገጠሬ ሴቶችን ታድጓል ትምህርትን አዳርሷል ነው ጥያቄው።……እዚህ ሃገር ሁልግዜ ጋሪው ከፈረሱ እንደቀደመ ነው ከተሜና ትምህርት ቀመስ ሴቶቹ አክራሪነትና ወንድን መጸየፍ ጀምረዋል። ህጉ ቀፍድዶኝ ነውንጂ እችላለሁ ትላለች ጥሩ ነው ገጠሬዋ ገና ስለብልት መተልተል በቂ ስልጠና አልተሰጣትም በወሊድ ትሞታለች ለመማር ትጠራሞታለች እንደው መጀመሪያ እነዚህን ማዳን አይቀድምም? አክራሪ ሴታዊነት ስልጣኔስ ከሆነ ለብቻ ከሚሆን እህቶቻችሁን ይዛችሁ አይሻልም?

Share.

About Author

Leave A Reply