ውድ ሀጫሉ ራስህን አታስገምት !

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

እናቱ የሞተችበትና ወደ ገበያ የሄደችበት እኩል ይለቅሳሉ ነው አያለቅሱም የሚባለው ? በከሸፈው የቤተመንግሥት ጥሪ ላይ ከተከፉት መሀል የጥሪ ወረቀት የደረሰው ተወዳጁ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ አንዱ ሆኗል ፡፡ ሌሎች ብዙዎች ከጠሪዎቹ የተሻለ ጥበባዊ አስተዋፅኦ ያላቸው ሙያተኞች ደግሞ ጭራሽ በሩን እንዲረግጡም ያልተፈቀደላቸው ናቸው ፡፡ ተረቷ የምታስፈልገው እዚህ ጋ ነው ፡፡

ድምጻዊውን ያስከፋው ከብዙዎቻችን የተለየ ነው ፡፡ አጠራሩ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እዚህ ለመናገር የሚያፀይፉ ግድፈቶች ቢኖሩበትም አንዱም ምክንያት ከቋንቋ ፣ ብሔርና ፖለቲካ ጋር የተያያዘ አይደለም ፡፡ ከጠሪዎቹ በላይ ሀጫሉ ነው የብሔር መልክ የሰጠው ፡፡ ብዙዎቻችን ሳንጠራ የቀረነው ወደፊት በምንረዳቸው የተለያዩ ምክንያቶች እንጂ በብሔራችን ወይም ፖለቲካዊ አቋማችን አይደለም ፡፡ ጠሪዎቹ እዚያ ድረስ ርቀው የሚሔዱ አይመስለኝም ፡፡

መገፋፋት ባለበት በር ላይ ሀጫሉ የተጠሩት የኦሮምኛ አርቲስቶች አምስት መሆናቸውን በምን እርግጠኛ ሆነ ? ቀድመው የገቡ ወይም ዘግይተው የሚመጡ ቢኖሩስ ? ሀጫሉ በኦሮምኛ የሚዘፍን የመላው ኢትዮጵያውያን ልጅ ነው ፡፡ ራሱን አጥብቦ መስፋት የለበትም ፡፡ የብሔር ተዋፅኦ ቢያስፈልግ እንኳ ኦሮሞ አርቲስቶች እንዳለውም 5 ብቻ ይሁኑ ፡፡ ከትግራዋይ አርቲስቶች ስንት ተጋብዘዋል ? ከደቡብስ ? ከሀረርስ ? ከሌላውስ ? እዚህ ዝርዝር ውስጥ መግባት ከአንድ እውቅ የጥበብ ሰው የሚጠበቅ አይደለም ፡፡ ከበር ተመልሶ ትኩረት ለመሳብ ከመሞከርና ገብቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት እድሉን ስለተነፈጉቱ ከመጠየቅ የቱ ነው ውጤታማው ?

ሀጫሉ የተናገረውን ይዛችሁ ‘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ አርቲስቶችን ለብቻቸው ሊያናግሯቸው ይገባል ” ያላችሁትም ሀሳባችሁን እንደገና ብትመረምሩት መልካም ነው ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜው እንኳ ቢኖራቸው ሊይደርጉት አይገባም ፡፡ የሌላው ብሔር ብሔረሰብ አርቲስቶችንስ አስባችኋቸዋል ? ሁሉን በየተራ ቢያናግሩ ደግሞ ስራቸው ምን ሊሆን ነው ? ጎበዝ ከቋንቋ ማንነት ውጡ ፡፡ ሀጫሉም ራስህን አታስገምት ፡፡ አንተ ትልቅ ነህ ፤ ሰፊ ነህ ፡፡ እወቀው ፡፡

 

Share.

About Author

1 Comment

  1. Hacaalu is a talented artist and  one of the brilliant heroes of the Oromo nation like Fayissa Lelisa and Wario Gemeda. The whole Oromo nation is proud of Hacaalu! 

Leave A Reply