ውጭ ሃገር የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ ዲያስፖራ ና የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +
በውጭ ሃገር የሚኖሩ አብዛኞቹ ኢትዩጵያዊያን በውጭ ሃገር የሚኖሩት አንድም ዜግነታቸውን ለውጠው አልያም በጥገኝነት በሚኖሩበት ሃገር ህግ መሰረት የመኖርያ ወይም የስራ ፍቃድ (Residence Or Work permit ) በማግኘት / በመያዝ መሆኑ ይታወቃል ( አብዛኞቹ )።
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ስልጣን ከያዙ በኃላ በውጭ ሲንቀሳቀሱ ( በሃገር ውስጥ ሳይመዘገቡ ) የነበሩና ከፍተኛ የዲያስፖራ አባልና ደጋፊ ያላቸው ድርጅቶች ሃገር ውስጥ በመግባት በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በምርጫ ቦርድ መመዝገብ እንደሚኖርባቸው ይታወቃል ( ምርጫ ቦርድ እንደተቋም ያለበት ጥያቄም ልብ ይሏል ) ።
ይህ በዚህ እንዳለ እስካአሁን ባለው ሁኔታ በሃገር ውስጥ የሚመዘገብ ፖርቲ አባላት የሚወስነው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ 573/2000 ያልተሻር ወይም ያልተሻሻለ በመሆኑ ( በዜግነት ኢትዩጵያዊ በአኗኗርም በሃገር ውስጥ መደበኛ ነዋሪ መሆን ይኖርበታል የሚለው ) ዲያስፖራውን ከሃገሩ የፓርቲ ፖለቲካ የሚያገል አሰራር እርምት ያላገኘና የተዘነጋ ሆኖ ይገኛል ።
በመሆኑም ከፓርቲ ምዝገባ ውትወታ ባሻገር ለፓርቲና ለአባላቱ ህጋዊ መብትን የሚገደቡ የተለያዩ አፋኝ ህግና አዋጆችን ጨምሮ የፓርቲ ምዝገባ አዋጅ በአስቸኴይ ሊሻሻል /ሊለወጥ ይገባል ።
ከበርካታ ምክንያቶች የተወሰኑ ዋና ምክንያቶች ብናነሳ :
1ኛ : አዋጅ 573/2000 በተለያየ ምክንያት በስደት የሚኖሩ ኢትዩጵያዊያን ከፓርቲ ፖለቲካ ተሳትፎ ያግዳል
( የጥምር ዜግነት ያለመፈቀዱ እንዳለ ሆኖ
2ኛ. በውጭ ሃገር በመኖር ሃገር ውስጥ መደበኛ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ፓርቲ ማደራጀትም ሆነ አባል መሆን ህገወጥ ያደርጋል ።
3ኛ. ፖርቲዎች ከውጭ ሃገር ገንዘብን ጨምሮ ምንም ዓይነት ድጋፍ መሰብሰብ አይችሉም ….ወዘተ
በሌላ በኩል ይህ አዋጅና መሰል ህጎች ከወዲሁ መለወጥ ካልቻሉ በቀጣይ ጊዜያት ዲያስፖራው ከፓርቲ ፖለቲካ ተሳትፎ አንድ ደረጃ ዝቅ ብሎና ተገፍቶ በአጃቢ ማህበርነት (በይፋ ለፓርቲ ድጋፍ ማድረግ ሳይችል ) እንዲጫወት ይወሰንበታል ማለት ይሆናል ።

Share.

About Author

Leave A Reply