ዛሬ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የአዲስ አበባ መንገዶች በጎርፍ ተዋጡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከመገናኛ እስከ ሳህሊተ ምህረት አደባባይ ድረስ ያለው መንገድ ዛሬ በዘነበው ከባድ ዝናብ አማካኝነት የጎርፍ መጥለቅለቅ ደረሰበት።

ይህ የባቡርና የመኪኖች ጥምር መንገድ የሆነው አካባቢ የጎርፍ መውረጃ ችግር እንዳለበት ይነገራል። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጥኡማይ ወልደገብርኤል ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት አካባቢው ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ በሚደርሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።

በመሆኑም መንገዱን የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ተለዋጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ነው ዳይሬክተሩ ያሳሰቡት።

በመንገዱ ዙሪያ ያሉትን የውሃ ማፍሰሻዎችን ለመስራትም አስቸጋሪ የሆነው የባቡር መስመሩ እንደሆነ የገለጹት ባለስልጣኑ ወደፊት ለመስራትም ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

በመሆኑም አካባቢው ዝናብ ሲጥል የጎርፍ መጥለቅለቅ ስለሚያጋጥመው በተለይም በሌሊት የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ዝናብ ከዘነበ መንገዱን መጠቀም እንደሌለባቸው እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply