የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት በተነሳባቸው ተቃውሞ ሳቢያ ክልሉን ጥለው መሸሻቸው እየተነገረ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት ሙራድ አብዱልሀድ በተነሳባቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ሳቢያ ክልሉን ጥለው መሸሻቸውን የቃሊቲ ፕሬስ ምንጮች ተናግረዋል።

እንደ ምንጮቻችን ከገለጻ ከሆነ ግለሰቡ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተያዙ የሚል ወሬም በአካባቢው እየተናፈሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሬዚዳንቱ ቢሮ በከፍተኛ የወታደር ሀይል እየተጠበቀ ነው።

ሌላ የቃሊቲ ፕሬስ ምንጭ ደግሞ “የፖሊስ ኮሚሽነሩ ነው (የኦህዴድ ሰው ነው) የክልሉ ፖሊስ ምንም አቅም አጥቷል ። የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስረዲን አሊን የፖሊስና ልዩ ሀይል አልታዘዝ ብለውት ትናንት “ሌባ ሌባ :እያሉ ሰድበው ከቢሮው አባረውታል። በመኪና ነው አምልጦ የወጣው። (ይህንን በአይኔ አይቻለሁ) ሰውየው ሰሞኑን ሰልፍ ይደረጋል ከመባሉ ጋር ተያይዞ..ፖሊሶችን “ቀጥቅጡ እርምጃ ውሰዱ ሲል በፖሊሶችና ልዩ ሀይል እምቢ በማለታቸው አጸያፊ ስድብ አዝንቦባቸው ነበር። ትጥቃችሁንም አስቀምጡና ውጡ ብሎ ነበር።” በማለት ስለ ሁኔታው አብራርተዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply