Thursday, January 17

የህወሃት/ኢህዴግ ንብረቶች እያሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ሃብትና ተቋማት አይሸጡም።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚታገሉና ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖሩ እና እልፍ አእላፍ የህዝብ ንብረት በእጃቸው የሚገኝ የኢህዴግ አባል ድርጅቶች ንብረቶች እያሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቶ አመታት በላይ ጥሮ በጋራ ያፈራቸው የህዝብ ተቋማትና ንብረቶች በፍፁም አይሸጡም። አይለወጡም። እጅ አይቀይሩም።

የሌሎች የኢህዴግ ሶስቱ እህትማማች ሴቶች ንብረቶች ሳያስፈልግ የሃብቷሟና የታላቋ ሴት እህታቸው የህወሃት ንብረት ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ የገንዘብ ችግር ቢያንስ ለሚቀጥሉት አስር አመታት ለመፍታት በቂ ነው።

ህወሃት እራሷ ላለፉት 27 ዓመታት ደጋግማ በአክሱም ፅዮን እየማለችና እገዘተች እንደነገረችን ለኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለችና ለዚህ ህዝብ የሚትኖር፣ ለዚህ ህዝብ የሚትሞት፣ ከግንቦት 20 1983 ዓም ጀምራ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጄራ እናት የሆነች የኢህዴግ ትልቋና በጣም ሃብታሟ ሴት ነች።

ይቺ ህወሃት የሚሏት ሴት ለህዝብ እየሞተችና እየኖረች ከመሆኗም በላይበ በከፊል መንግስት ሆና፣ በከፊል ደግሞ የፓላቲካ ፓሪቲ ሆና፣ በሌላ በኩል ደግሞ ነጋዴ ሆና፣ መንግስትነቱ፣የፓላቲካ ፓርቲነቱና ነጋዴነቱ አንድም የጥቅም ግጭት ሳይፈጥሩበት በአንዴ ሁሉን በመቆጣጠሯ ከፍተኛ ሃብት በእንጄራ እናትነቷ ለሚትታገልለት የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ያከማቸች ብርቱ ባልቴት ነች።

እቺ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳትወልድ በአጋጣሚ የኢትዮጵያ ህዝብ የእንጀራ እናት የሆነች ባልቴት እያለች፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የውጭ ሚኒዛሪ በማጣት የፊጆታ እቃዎችን እንኳን ከውጭ የሚያስገባበት የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ የሚያጣበት ምንም ምክንያት የለም።

መቼም የኢትዮጵያ ህዝብ የእንጄራ እናት የሆነችው ህወሃት ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም በ EFFORT ፣ በ REST ፣ በTDA እና በተለያዪ በአገር ውስጥና በውጪ በተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶች ያከማቸችው ሃብቶች እያሉ ለህዝብ ታጋይዋና አንድ እግሯ ከመቃብር ጉድጓድ የደረሰው ህወሃት ሞታ ትቀበራለች እንጂ 76 ሚልዮኑ ገና ወጣት የሆነው ኢትዮጵያ ህዝብ አይሞትም።

 

የእንጄራ እናታችን ህወሃትም ብትሆን ሞታ ትቀበራለች እንጂ በቀን አንዴ እንዲበሉ አድርጋ በረሃብ ያኖረቻቸውን የምትወደው ህዝቧ እንዲሞት ጨካኝ ልቧ አይችልም።

 

ስለዚህ በዚህ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያን ህዝብ ከገባበት የውጭ ምንዛሪ ችግር ለማዳን ህወሃት ሁሉንም የንግድና ድርጅቶቿን ሽጣ ለሚትወደውና ለሚታገልለት የእንጄራ እናቱ ለሆነችው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እንዲውል ማድረግ የባልቴቷን ፍቃድ አይጠይቅም።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይም የእንጄራ እናታችንን ንብረቶች ሽጦ ለህዝብ ጥቅም የማዋል ሙሉ ውክልና አለው።

ይህ ብቻ አይደለም። የእንጄራ እናታችን ህወሃት የኢትዮጵያን ህዝብ ደህንነትና ሃብት ለመጠበቅ በአለም የተመሰከረለትና የሌቦችን መንገድ ሁሉ የሚያውቅ እና ከሌቦች ሁሉ የሚበልጥ የመከላከያና የደህነት ኃይል ገንብታለች

ይሁን እንጂ በአንድ Global Financial Integrity ጥናት መሠረት የሌባ አዳኙ የህወሃት ኃይል እያወቀው ከ2004 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ብቻ 25 ቢልዮን የአሜርካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ህወሃት በሚታውቃቸው የውጭ ባንኮች አሉ።

እንደ የተከበሩ አለማየሁ ገዳ የሚባሉ ኢኮኖሚስት በጥናት እንዳረጋገጡት ደግሞ ከ1991 እስከ 2004 ባለው አስራ ሶስት አመት 13 ቢሊዮን የአሜርካ ዶላር ተሰርቆ ከኢትዮጵያ ወጥቷል። ጠንካራው የህወሃት የመከላከያና የደህንነት ኃይል ይህም ገንዘብ የት እንዳለ ያውቃል።

ከ2013 እስከ 2018 ባለው አምስት አመታት ጊዜ ደግሞ ቢያንስ በአመት ከሁለት ቢልዮን ያላነሰ የአሜርካን ዶላር ህወሃት ብቻ በምታውቃቸው አማጋጮቿ ተዘርፎ ከአገር ጠፍቷል። ይህ ገንዘብ ወደ 10 ቢልዮን ዶላር ይሆናል።

በአጠቃላይ ባለፉት 27 ህወሃት የኢትዮጵያ ህዝብ የእንጄራ እናት ሆና በቆየችባቸው ክፉ አመታት ቢያነረስ ወደ 48 ቢልዮን የአሜርካን ዶላር ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ተሰዷል።

ይህ ትልቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ህወሃት ብትነግድበት ልያስገኝ የሚችለው ወለድና ትርፍ ሳንጨምር በዛሬ ተመን ወደ ኢትዮጵያ ብር ስንመልሰው አንድ ነጥብ ሰባት ትርሊዮን የኢትዮጵያ ብር ይሆናል።

ይህ እንግድህ የእንጄራ እናታችን ህወሃት ሞግዚቶቻችን አድርጋ ከሰየመቻቸው ሶስት ታናናሽ እህቶቿዋ እና ምንነታቸው ያልታወቁ ሌሎች ሴት ሞግዚቶች እጅ ያለውን መጠነኛ ሃብት ሳንጨምር ነው።

ስለዚህ ህወሃትን የመሰለ በአንዴ መንግስትም፣የፓላቲካ ድርጅትም፣ ነጋዴም ሆኖ ሁለገብ ትግል ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲታደርግ የኖረች ሃብታምና ህይወቷን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለመሰዋት የቆራጠች ባልቴት ንብረት እያለ የኢትዮጵያ ህዝብ የውጪ ምንዛሪ ችግር ብሎ ነገር የለም። መኖርም አይችልም።

ስለዚህ ምንም ፍቃድ ሳያስፈልግ የዚህ ለህዝብ የሚትኖረውና የሚትሞተው የህወሃት ንብርቶች በየሉበት ተሽጦ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል መድረግ ይገባል።

ነገር ግን ልክ ግንቦት 20 ላይ እንደሆነው ዜናው በጥሩ አማርኛ ጥሩ ተደርጉ “ህወሃት ሲትጠቀምበት የነበረው ሃብት ሁሉ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥጥር ስር ውሏል።” ተብሎ ኢሳትና ኦመነን ጨምሮ በሁሉም ሚዲያ እንዲነገር ማድረግ ይገባል። የመሸጫቸው ቀንም ሳይደርስ ከወዲሁ ነገሩን ለህዝብ ማስገንዘብ አስፈላጊ ነው።

(ብርሀነ መስቀል አበበ)

Share.

About Author

Leave A Reply