የሐረሪ ብሄረሰብ አባላት የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ እኛን አይወክልም በማለት ጊዜያዊ ባለ አደራ ኮሚቴ አቋቋሙ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ አመራሮች ለ 27 አመታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ብሄረጸቦች በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰ የሚገኝው ፋሺስታዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ መቆም እንዳለበት ዛሬ በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ ቁጥራቸው ከ 600 በላይ የሚሆኑ የብሔረሰብ አባላት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ በሙሉ ድምጽ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ እንደማይወክላቸው ገለጹ።

የቀድሞውን የፖርቲው ሊቀ-መንበር የነበሩት እና ከድርጅት ተባረው የነበሩት አቶ ዘይዳን በክሪ የግዜያዊ ባላደራ ኮሚቴ ሰብሳቢ በማድረግ እንዲሰሩ ሲመደብ ሌሎች 20 የኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።

የብሄረሰብ አባላት ባወጡት የአቃም መግለጫ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ብሄረሰብን ወክሎ በየትኛውም መድረክ እንዳይሳተፍ እንዲሁም ለዘመናት በፍቅር አብሮ የኖሩ የኦሮሞ ህዝብ ማንም ሊለያቸው እንደማይችልና ግንኙነታቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወስነዋል።”

Share.

About Author

Leave A Reply