የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከኮሚሽኑ አባላት ጋር በአሰራር ዙሪያ ውይይት አካሄዷል፡፡

የኮሚሽኑ አባላት ባካሄዱት ውይይት በተለይ ሙስና፣ ፍትሃዊ ያልሆነ ስምሪት፣ የጥቅማ ጥቅም አለመከበር እንዲሁም ከማዕረግ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያለባቸውን ተጽዕኖ በውይይቱ አቅርበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ወንጀሎች እንዳይከሰቱ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የፖሊስ አባለቱ ከፍተኛ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ የገለፁት የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ጀማል አህመድ በኮሚሽኑ አባላት ጥያቄ መሰረት በተደረገው የውይይት መድረክ የተነሱ የውስጥ መልካም አስተዳደር ችግርና ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ የተነሱ ጥያቄዎች በህገ አግባብ ይፈታሉ ብለዋል፡፡

በውይይቱም ችግሩን በሂደት ለመቅረፍ ከአባላቱ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀው አባላቱ ያካሄዱት ሰላማዊ ውይይት እንጂ የስራ ማቆም አድማ እንዳልሆነም አስረድተዋል።

አባላቱም የተሰጣቸውን ኃላፊነት ሞያዊ ስነ-ምግባሩን በተላበሰ መልኩ መወጣት እንደሚገባ ም/ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡

ከአባላቱ የተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ እስኪያገኙ ድረስም የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩን ስራ ምክትል ኮምሽነሩ ደርበው እንዲሰሩ ከመግባባት ተደርሶል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በከተማው የክልሉ ፖሊስ አባላት መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply