የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚሻውን ጉዳይ በተመለከተ ለፌ/ም/ቤት የውሳኔ ሃሳብ ቀረበ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ መጋቢት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ የአስራ ስድስት አቤቱታ አቅራቢዎችን መዝገብ በመመርመር በአንዱ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው በመሆኑ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ አስራ ሦስቱን ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት ውሳኔ ሰጥቶ ሲዘጋ ቀሪ ሁለት መዝገቦች ላይ ደግሞ የተለያዩ ሀሳቦች ከተንሸራሸሩና ክርከሮች ከተደረገባቸው በኋላ ተጨማሪ ማጣራት እንዲደረግባቸው በይደር አልፏቸዋል።

ለሕገ መንግሥት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ የቀረበበት መዝገብ በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሁለት አንቀጾችን ማለትም አንቀፅ 13(1) ላይ የተደነገገውን የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎቱ በሕገ መንግስቱ በተሰጠው ግዴታ መሰረት የአመልካችን ሕገ መንግስታዊ የንብረት መብቶችን አለማክበሩ እንዲሁም አንቀፅ 40 (1) እና (7) ላይ ሕገ መንግስታዊ የንብረት ባለቤትነት መብት ጥሶ የተገኘ ነው በማለት ሲሆን፣ ጉባዔው በይደር ያለፋቸውን መዝገቦች ጨምሮ ሌሎች መዝገቦችን በቀጣዩ ጉባዔ ለማየት ቀጠሮ ይዟል።

(ምንጭ፡- የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት)

Share.

About Author

Leave A Reply