የመንግስት መስሪያ ቤቶች 90 ከመቶ የአንድ ብሄር ሰዎች እየሞሉት ነው! ካሁኑ ለምን እንበል!

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በአንድ የመንግስት (ፌደራል) መስሪያ ቤት ውስጥ ስመላለስ ነበር:: ወደ ስድስት የሚጠጉ የዲፓርትመንት ሃላፊዎችን ለማናገር ችያለሁ:: ከስድስቱ ውስጥ አምስቱ ኦሮሞ ናቸው :: (የድጋፍ ሰራተኞችን ሳላካትት ማለት ነው):: ይህን መስሪያ ቤት ከዚህ በፊትም ስለማውቀው ድሮ በህውሃት ዘመን እንኳ እንዲህ 90 % በአንድ ብሄር ውስጥ ተጽዕኖ ውስጥ ወድቆ አይቼ አላውቅም::

በግሌ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ወርዱንና ቁመቱን በሚመጥን አኳኋን አይደለም በፌደራል በሌሎች የሃገሪቱ ክፍል እንኳ የሚገባውን ውክልና እንዲያገኝ ስለታገለ ቢያገኝ መልካም ነው: ተገቢም ነው:: ሆኖም ህውሃትን በኦዴፓ የሚተካ አካሄድ ተመልሶ አዙሪት ላይ የሚከተን እንጂ ወደፊት የሚያስሄደን አይሆንም:: ከእንግዲህ ሌሎች ብሄሮች የይሉኝታ አካሄድ አቁመው እያንደንዱ መስሪያ ቤት (ያው መቼም በብቃት ሳይሆን በብሄር ተዋጾ ብቻ እየሆነ ስለሆነ) ኢትዮጵያን በሚመስል መልኩ እንዲዋቀር ሊታገሉ ይገባል::

በነገራችን ላይ ያናገርኳቸው ሁሉም ሃላፊዎች በአግባቡና በትህትና ስላስተናገዱኝ ምስጋናዬ ይድረሳቸው (ያው ለጉዳዬ አንድም መፍትሄ መስጠት ባይችሉም):: ሆኖም ህውሃቶች ወደ ስልጣን ሲመጡም እንዲህ ትሁት ነበሩ: በአግባቡ ቁጥጥር ያልተደረገበት የስልጣን ድንበር በኋላ ትዕቢተኝነትና የማን አለብኝነትን ካባ አላብሷቸው ሃገሪቱን አሁን ወደገባችበት የፖለቲካ አዘቅጥ ከተዋል::

ስለዚህ የእነዚህን ሃላፊዎች ትህትና መደገፍ ሳይሆን በህግ የበላይነት ላይ ነው መተማመን የምፈልገው:: ሃገሬ በማንም የግለሰብ ቅንነትና ትህትና ላይ ሳይሆን በህግ መከታነትና በእኩልነት ወደፊት የምስተናገድባት ምድር ነው እንድትሆን የምፈልገው:: በነገራችን ላይ አቶ ታከለ ኡማ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የክፍለ ከተማ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሄር እየሞሉ ነው የሚል ሃሜት የትም ቦታ ስሰማ ነው የቆየሁት (ትክክል ይሁን የተጋነነ ሄጄ አላረጋገጥኩም):: ይሁንም እንጂ ህዝብ ካለምክንያት እንዲህ ስለማያወራ ስህተት እንኳ ከሆነ አስተሳሰቡን በቶሎ ማረም ተገቢ ነው:: ካልሆን የህውሃት ፋንታ ሁሉንም ይደርሰዋል::

(ዞላ ሞገስ)

Share.

About Author

Leave A Reply