“የመከዳት ስሜት እየተሰማኝ ነው” ጌታነህ ሃ/ሚካኤል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት በተደረገ የጨፌ ኦሮሚያ የእርቅ ህዝባዊ ሸንጎ ላይ አቶ ለማ መገርሳ “ተናግሮታል” የተባለ ከድምፅ የተተረጎመ ጽሑፍ (ዶ/ር አብርሃም አለሙ እንደተረጎመው) ከታማኝ ምንጮች ሳይቀር ተልኮልኝ አንብቤው ነበር:: ነገር ግን ራሴ ኦሪጅናል የኦሮሚፋ ንግግሩን የያዘውን ቪዲዮ አግኝቼ እስካደምጠው አላምንም ብዬ ነበር:

ዛሬ በጥልቅ የሀዘን ስሜት ውስጥ ሆኜ በጠቅላይ ሚንስትሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ ላይ ኦቦ ለማ መገርሳ በኦሮሚፋ ያደረጉትን ንግግር በጥሞና አድምጬዋለሁ::

1) የኦዴፓ እቅድ በዲሞግራፊ ለውጥ የከተማ ፖለቲካን መቆጣጠር ከሆነ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ሊሆንበት አይችልም !

2) ኦዴፓ ከተሞችን “የመውረር” እቅድ ካለው ወደፊት ከተሞች ለዜጎች ሠላም የሰፈነባቸው የጋራ የመሥሪያ እና የመኖሪያ ቦታ መሆናቸው ጥያቄ ውስጥ የሚወድቅ ይመስለኛል !

3) የሽግግሩን ፖለቲካዊ አካሄድ በጥርጣሬ የሚመለከቱ ወገኖችን በጅምላ መውቀስ ትክክል ያለመሆኑን ተረድቻለሁ !

4) “ቲም ለማ” በብዙኅኑ ልብ ውስጥ ያለው (virtual) ቦታ እና በእርግጥ (actual) መሬት ላይ ያለው እውነት እንደሚለያይ ተረድቻለሁ !

5) በግልጽ ቋንቋ የመከዳት (betrayed) ስሜት ተሰምቶኛል !

በመጨረሻም የዛሬ ዓመት አካባቢ የወልድያ ወጣቶች ለውጡን ደግፈው ሰልፍ በወጡበት ወቅት ይዘው በወጡት መፈክር ልሰናበት …

“የወደድንህ ኢትዮጵያን ስለወደድክልን ነው”

Share.

About Author

Leave A Reply