የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመድን ሥራ እና በአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቆችና የተለያዩ የብድር ስምምነቶች ረቂቆች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመድን ሥራ እና በአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቆችና የተለያዩ የብድር ስምምነቶች ረቂቆች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 72ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፤ ውሳኔዎችንም አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በብሔራዊ ባንክ ተዘጋጅተው የቀረቡትን የመድን ሥራ አዋጅ እና የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ አዋጅ ማሻሻያ አዋጆች ተመልክቷል፡፡ አዋጆቹን ማሻሻል ያስፈለገው በውጭ ሀገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ተወላጅ የውጭ ዜጎች በፋይናንስ ዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያዬ በኋላ እንዲጸድቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ታውቋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዘጋጅቶ ያቀረበውን የማረሚያ ቤት ረቂቅ አዋጅም ተመልክቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የማረሚያ ቤቶችን የእስረኞች አያያዝ ሁኔታና አጠቃላይ ገጽታ ለማሻሻል የሚያስችል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ ምክር ቤቱ በዚህኛውም ረቂቅ ላይ በሰፊው ከተወያዬ በኋላ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የቀረቡ የተለያዩ የብድር ስምምነቶችና የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ72ኛ መደበኛ ስብሰባው ተመልክቷል፡፡ ከውይይቱ በኋላም የተገኙት ብድሮች ከኢትዮጵያ የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ እና ጫናቸው ያልበዛ በመሆኑ እንዲጸድቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቁን አስላልፏል፡

Share.

About Author

Leave A Reply