የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል፤ ውሳኔዎቹንም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመምራትና ሥራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተለያዩ የብድር ስምምነቶችን ረቂቆች አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፤ የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ እና የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎትም በአንድ ኤጀንሲ እንዲደራጁና ሥራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ በ63ኛ መደበኛ ስብሰባው ትናንት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረትም ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ድጋፍ መርሀ-ግብር ማስፈጸሚያ በኢትዮጵያ እና በዓለማቀፍ የልማት ማኅበር መካከል፣ ለሴቶች ንግድ ሥራ ፈጠራ ብቃት ማሳደጊያ መርሀ-ግር ማስፈጸሚያ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ከተሞች ሥነ-ንጽሕና መሠረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ መርሀ-ግብር ከፊል ማስፈጸሚያ በኢትዮጵያ እና በጣልያን መንግሥት መካከል እንዲሁም ለዘላቂና አካታች የግብርና ምርት እሴት ሰንሰለት ዕድገት መርሀ-ግብር ማስፈጸሚያ በኢትዮጵያና በጣልያን መንግሥት መካከል የተደረጉ የብድር ስምምነቶች ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፡፡

ምክር ቤቱ የዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ስልጣን፣ ተግባርና አደረጃጀትን ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ላይም ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የኢሜግሬሽንና የዜግነት ዋና ጉዳይ መምሪያ፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ እና የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት አሰጣጥ ከሥራ ባሕሪያቸው አንጻር በአንድ ኤጀንሲ እንዲደራጁ በመደረጉ የኢሜግሬሽን፣ የዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ስልጣን፣ ተግርና አደረጃጀትን ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ማሻሻያዎችን በመጨመር ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት

Share.

About Author

Leave A Reply