የሪታ ፓንክረስት የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን ማክሰኞ ይፈፀማል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአንጋፋው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክረስት ባለቤት የሪታ ፓንክረስት የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን ማክሰኞ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡

የሪታ ፓንክረሰት የቀብር ስነ ስርዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበተት ነው ማክሰኞቹ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ የሚፈፀመው፡፡

የሪታ ፓንክረስት ህልፈተ ህይወት ሀሙስ ምሽት አንደተሰማ የሚታወስ ነው፡፡ ሪታ ፓንክረስት ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ በተቋማት ግንባታና በተለያዩ ስራዎች ላይ አሻራቸውን ማሳረፋቸው ይነገራል።

ከዚህ ባለፈም ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ሬሚነሰንስ (”Ethiopian Reminiscences,’’ ) በግርድፍ ትርጓሜው የኢትዮጵያ ልምድና ታሪካችን የተሰኘ መፅሃፍን አበርክተዋል፡

ይህ መፅሃፍ በኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ1950 እና 1960ዎቹ የነበሩ ትልልቅ ህዝባዊ ሁነቶችን የሚሳይ ነው፡፡ ሪታ ፓንክረስት በ92 አመታቸው ነው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply