“የሰቆቃ ድምጾች” የጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው አዲስ መጽሀፍ ታተመ። የፊታችን ቅዳሜ ገበያ ላይ ይውላል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ላለፉት ሁለት አመታት በኢትዮጵያ የማሰቃያ ወህኒ ቤቶች በግፍ ሲማቅቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በየፍርድ ቤቱ በመከታተል በማህበራዊ ድረ-ገጽ ለህዝብ እንዲደርሱ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የመጀመሪያ መጽሀፉን ለህትመት አብቅቷል።

“የሰቆቃ ድምጾች” የተሰኘው ይሄው አዲስ መጽሀፍ የተለያዩ የፖለቲካ እስረኞችን የእስር ቤት ቆይታና የፍርድ ሂደት የተካተተበት መሆኑን ገልጿል።

ጌታቸው እንደገለጸው በእስር ቤት የተገደሉትና የጠፉት ጉዳይ በመጽሀፉ ተጠቃልሏል። የቂሊንጦ ቃጠሎ ምክንያት፣ ከቃጠሎው በኋላ በእስረኛው ላይ የተፈፀመው ዘግናኝ ቅጣት፣ የእስር ቤት ታሪኮች፣ የዳኞችን አይን ያወጣ አድሎ፣ የፍርድ ቤት ውሎዎችን አጠቃልየበታለሁ፣ እስር ቤቱን የሞሉት የትህነግ/ህወሓት ታጋዮች ጉዳይና መሰል ጉዳዮች ተጠቃልለዋል” ብሏል።

መጽሀፉ በቀጣይ አርብ ወይ ቅዳሜ ገበያ ላይ ይውላል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply