የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር ቤት ለማፍረስ እቅዱን ጨርሶ የነዋሪዎች ቤት ላይ በቀይ ቀለም የኤክስ ምልክት እየቀባ ይገኛል ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር ልክ እንደ ለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ብሔር ተኮር በሆነ መልኩ ቤት ለማፍረስ እቅዱን ጨርሶ ወደ ትግበራ ሊገባ የነዋሪዎች ቤት ላይ በቀይ ቀለም የኤክስ ምልክት እየቀባ ይገኛል ።

በለገጣፎ ያጋጠመው የዜጎች ሰብዓዊ ቀውስ ዛሬም ድረስ መፍትሄ ማግኘት አልቻለም ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች የሰው እጅ እየጠበቁ በቤ_ተዕምነት ተጠልለው ይገኛሉ ። ልጆቻቸው ትምህርታቸው ሳይወድ በግድ ለማቆም ተገደዋል ይህ ሰብዓዊ ቀውስ መንግስት አይቶ እንዳላየ ሳምቶ እንዳልሰማ ዝምታን መርጦ ዜጎች ለችግር ተጋልጠዋል።

ቤታቸውን ያፈረሰችው ባለስልጣን የዘረጉትን ድንካን ሳይቀር አስፈርሳ ያስጠላሏቸውን የቤተ ዕምነት አባቶች ሳይቀር የከተማውን ገፅታ ያበላሻሉና አስወጧቸው በማለት እያስፈራሩ ይገኛል ።

ይህ ሰብዓዊ ቀውስ መፍትሄ ሳያገኝ በላዩ ላይ የሌሎች ዜጎችን መኖርያ ቤት በስመ ህገ ወጥነት ለማፍረስ መዘጋጀት ተገቢነት የሌለውና ሀላፊነት ከሚሰማው ለዜጎቹ ግድ ከሚለው መንግስት የማይጠበቅ ድርጊት ነው ። ይህንንም ድርጊት ጠ/ሚ አብይ አልሰማውም ብለው እንዳያልፉ ከመፍረሱ በፊት ለዜጎቹ የመኖር ዋስትና ሊሰጡ ይገቧዋል ።
© ZewudeTadesse

Share.

About Author

Leave A Reply