የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በ9 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በ9 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በሀገሪቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ።

ምክር ቤቱ እስካሁን ከሱዳን ተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ሲያደርገው የነበረውን ድርድርና ስምምነት ወደ ጎን በመተው በዘጠኝ ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

ወታደራዊ አስተዳደሩ ይህንን ያለውም በሱዳን መዲና ካርቱም ሰልፈ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ በወሰደው እርምጃ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ውግዘት ከደረሰበት በኋላ ነው ተብሏል።

የፀጥታ ሃይሉ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃም እስካሁን ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።

Share.

About Author

Leave A Reply