የሲዳማ ሕዝብ እሴቶች በሀገሪቱ ያሉ መቃቃሮችን በመፍታት የነገይቱን ኢትዮጵያ ብሩህ ለማድረግ ጥቅም ላይ መዋል አለበት ተባለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የፊቼ ጨምበላላ የመጀመሪያው ቀን የሆነው ፊጣሪ በተለያዩ ስርዓቶች ሲከበር ውሏል፡፡የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ግለሰቦችም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባደረጉት ንግግር እንደጠቀሱት፤ የፊቼ ጨምበላላ እሴት የሆነውን ይቅር መባባልን በመጠቀም በየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ ያሉ መቃቃሮችን ይቅር በመባባል የነጋይቱን ህይወታችንና የነገይቱን ኢትዮጵያ ብሩህ ለማድረግ እጅ ለእጅ ተያይዞ ቀን ከሌሊት መስራት ያስፈልጋል፡፡

በዓሉ በውስጡ የሰላም፣ የመቻቻልና የአቃፊነት እሴት የያዘ ከመሆኑም ባሻገር ከሰው አልፎ እንስሳትና እፅዋት ጭመር እንክብካቤ የሚደረግበት መሆኑ በዓሉ የሰው ልጅ ስልጣኔ ጫፍ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በበኩላቸው፤ ፍቼ የዘመን መለወጫ ብቻም ሳይሆን በውስጡ ሰላምን፣ አብሮነትንና እርቅን ያቀፈ ነው ብለዋል፡፡ይህ ትል ቅርስ ነው፡፡

በዓሉ ልዩነቶችን በማክበር እውነተኛ የፌዴራል ስርዓት እንዲጠናከር ግብዓት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡ መቻቻልን ሰላምንና ፍቅርን በመስበክ ሀገሪቱ ለያዘቺውየብልፅግና ጉዞ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ብለዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply