የሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል ወጥቶ የራሱ ክልል የመመስረት ጥያቄ እንደሚያቀርብ የዞኑ አስተዳዳሪ ገለጹ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አክሊሉ አዱላ ዛሬ ማምሻውን በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ የሚከተለውን መግለጫ አስፍረዋል።

የተከበራችሁ በዞናችንና በከተማችን ሀዋሳ የሚትገኙ የሲዳማ ህዝብ፤ በስሜ ብዙ የፌስቡክ ገፆች ያሉ ቢሆንም ከዚህ ገፅ ውጪ ሌላ የለለኝ መሆኑን እያሳሰብኩኝ አሁን ስለሚንገኝበት ወቅት የሚከተለውን ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ወድጃለሁ፡፡

ውድ የሲዳማ ተወላጆች፤

እንደሚታወቀው በዞናችን የተለያዩ አጀንዳዎች እየተነሱ ህዝባችንን እያወዛገቡ ይገኛሉ፡፡ ይመስለኛል የመረጃ ክፍተት ሊሆን ይችላል፡፡

እንደሚታወቀው በሚዲያ የሚነገሩ ጭፍን ሀሳቦች ያሉ ቢሆኑም የአብሮነትንና ሀሳብ የመለዋወጥ ልማድ ሳይኖር ቀርተው እኛን የህዝብ ጠላት አድርገው የማየት ችግር ጎልተው ይታያል፡፡

ይሁንና ሲዳማ ክልል እንዳይሆን እንደአመራር ያደረግነው ትግል የለም፡፡ ምናልባት ማባበል ልሆን ይችላል፡፡ ሆኖም እንደ ደቡብ የተደራጀንበት አግባብ ጉዳዩን የሚያጓተት ከመሆኑ በስተቀር እኔም ሆንኩኝ ባልደረቦቼ ጥያቄውን ወዳለመቀበል አልደረስንም፡፡ ስለዝህ ነገና ከነገ ወዲያ የሚከበረውን የሲዳማ ህዝብ ታላቅ በዓል ያለምንም ችግር ማክበር ሲለሚያስፈልገን ሃሳባችሁን በተለመደው መልኩ በቄጣላ ማሳየት የሚትችሉ በመሆኑ ቅሬታችሁን ትታችሁ የፍቅር በዓላችንን እንዲታደምቁ አሳስባለሁኝ፡፡

ሲዳማ ክልል እንዳይሆን የሚከለክለው ነገር የለም ከሁኔታዎች በስተቀር፡፡ ያንንም ታግለን በመጪው ጊዜ በተደራጀ አመራር የሚመራ ሥርዓት እናዋቅራለን፡፡

ክቡር አቶ ሺፈራውና ሌሎች የፌደራል ባለስልጣናት ሀሳቡን የሚቃወሙ ባለመሆናቸው ጉዳዩን በመነጋገር እንዲንፈታ የተለመደውን ትብብራችሁን እጠይቀለሁ፡፡

በዛሬዉ እለት የሀዋሳ ዩኒቨሪስቲ ተማርዎች በነፃነት በተደራጀ መልኩና በደማቅ ሁነታ የፍቼ ጫምባላላ በዓላችን ማክበር መቻላቸዉ አስደስቶናል፡፡ ስለሆነም ከሁሉም ወረዳ ከነገ ጀምሮ የሚከበረዉን የሲዳማ ዘመን መለዎጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓላችንን ለማክበር ወደ ሀዋሳ የሚትመጡ የለምንም ሲጋት ደስታችሁን በቀጣላ እንድታደምቁ ጥሬን እያስተላልፍኩኝ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የብልፅግና እንድሆንላችሁ እመኛለሁን፡፡

አመሰገናለሁ!!!

አክልሉ አዱላ

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

Share.

About Author

Leave A Reply