የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች 1,202 ኪሎ አደንዛዥ እጽ ይዘዋል። ከአዘዋዋሪዎቹ መካከል 40 ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከተጠርጣሪ እጽ አዘዋዋሪዎች መካከል 40 ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል። የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች 1,202 ኪሎ አደንዛዥ እጽ በሳውዲ ድንበር ሊገባ ሲል መያዙን አስታውቋል ።

ይፋ የወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው በየብስና በባህር አደንዛዥ እጽ ይዘው ለመግባት የሞከሩትን ሴራ ማክሸፉን አስረድቷል። በደቡብ የሳውዲ ድንበር ከተማዎች አደንዛዥ እጽ ይዘው ለመግባት ሲሉ ከተያዙት አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎች መካከል 40 ኢትዮጵያውያን ፤10 የመናውያን ፤ 2 ፓኪስታን ፤ 2 ሶማሌና አንድ ሳውዲ እንደሚገኝበት የቃል አቀባዩ መግለጫው ያስረዳል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በድንበር ከተማዎች በአሲር እና በጀዛን ግዛቶች እስከ 400 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።

ነቢዩ ሲራክ

Share.

About Author

Leave A Reply