የቡናና ሻይ ባለስልጣን በከፋ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበትን የቡናን ስርወ መሰረት አስመልክቶ የሰጠውን መግለጫ አስተባበለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለቡና አምራች አካባቢዎችና ለፌስቡክ ተከታዮቻችን ይቅርታ ስለመጠየቅ !

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዘመናዊ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ልማትን የማረጋገጥ፣ዘመናዊ ህጋዊና ፍትሃዊ የግብይት ስርአት የመዘርጋት እና እሴት ለሚጨምሩ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ የመስጠት ተልዕኮዎችን በማሳካት የአምራቹንና የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በመረባረብ ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህን አላማዎች ለማሳካት ከአትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር እ.አ.አ ከዲሰምበር 3-5/2018 “International Coffee event in Ethiopia – The land of origins” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የቡና ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ በ United Nations Economic Commission for Africa(UN-ECA) የመሰብሳቢያ ማዕከል ከ 400 በላይ የውጭና በሺዎች የሚቆጠሩ የሃገር ውስጥ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት ሁነት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ሁነትም በዋናነት የቡናችን የተለየ ተፈጥሮዓዊ ጣዕምና የንጥረ-ነገር ይዘት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የሚቌቌም የቡና ልማት እያካሄድን ስለመሆኑ እና የተጀመረውን የቡና ሪፎርም የማስተዋወቅ ስራ ይከናወናል፡፡ ይህንን አለም አቀፍ ሁነት ለማስተዋወቅ በተለየዩ በፌስቡክ እና በድረ-ገጽ አድራሻዎች እንዲሁም ሜኒስትሪም መገናኛ ዘዴዎች እየሰራን ባለንበት ሂደት ከቡና መገኛ አካባቢ ጋር በተያያዘ የባለስልጣኑ ተልዕኮና አቋም ያልሆኑና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መልእክቶች በተለያዩ ቀናት መተላለፋቸውን የተገነዘብን በመሆኑ የባለስልጠን መ/ቤታችን አቋም ያለመሆኑን እየገለጽን ችግሩን የፈጠረውን አካል አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ሲሆን ለተፈጠረው የተዛባ መረጃ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን

Share.

About Author

Leave A Reply