የቡና መገኛ ባለቤትነት ላይ በተነሳ ተቃውሞ ከቦንጋ ወደ ጂማ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ዋለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቡናና ሻይ ሚ/ር ተወካዩ አቶ ሣኒ ረዱ የቡና መገኛን አስመልክቶ በሰጡት “የተሣሣተ” ነው በተባለ መረጃ የከፋ ዞን ርዕሰ ከተማ ቦንጋ ከባድ ተቀውሞ ተቀስቅሷል።

ከጅማና ከሚዛን ወደ ቦንጋ የሚያስገቡት መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል፡፡

የቡናና ሻይ ሚ/ር ዘንድሮ የሚከበረውን የቡና አለማቀፍ የቡና ቱሪዝም ከከፋ ዞን ጋር ለማድረግ ዝግጅቱን ከጨረሰ በኋላ በመሀል ላይ ባልታወቀ ሁኔታ ከጂማ ዞን ጋር እንደሚሰራ መግለጫ መስጠቱ ነው ከፍተኛ ተቃውሞ የተፈጠረው።

ይህን ቅሬታውን የዞኑ አስተዳደር ለሚመለከታቸው አካላት የጻፈው ደብዳቤ ዛሬ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ሲዘዋወር የነበረ ሲሆን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውንና ከማሻ፣ ሚዛን፣ ቴፒና ቦንጋ ወደ ጂማ ከተማ የሚወስደውን ዋና መንገድ መዝጋታቸውም ተነግሯል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply