የተከሰከሰውን አውሮፕላን በተመለከተ የደረሱን 4 አዳዲስ መረጃዎች!

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የተከሰከሰውን አውሮፕላን በተመለከተ የደረሱን 4 አዳዲስ መረጃዎች:: 1. የሟች ቤተሰቦች ካነሱት ጥያቄ በመነሳት አየር መንገዱ የሟቾችን ዲኤንኤ ውጤት የሚሰጥበትን ጊዜ አሳውቋል፡፡ በዛሬው እለት ከተለያዩ አገራት ለመጡት የሟች ቤተሰቦች የዲኤንኤውን የመጨረሻ ውጤት ለመግለፅ የስድስት ወር ጊዜ እንደሚያስፈልገው ነግሯቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ለቤተሰቦች የሞት ሰርተፍኬት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ 3. በነገው እለት(እሁድ) ጠዋት ለሟቾች የጅምላ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ፀሎተ ፍትሀት ይደረጋል፡፡

4. በአደጋው ስፍራ ኤክስቫተሮችና ከባድ የጭነት መኪናዎች እንዲመላለሱ መደረጉ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የሚያስችሉ መረጃዎችን ሊያጠፋ ወይም ሊሰብር ይችላል ሲሉ በቦታው ጉብኝት ያደረጉ አንድ ዲፕሎማት መናገራቸውን ሮይተርስ ዛሬ ዘግቧል፡፡

እኚህ ዲፕሎማት እንዳሉት አንዳንድ ፖሊሶች በቢጫ የታጠረውን የአደጋውን ቦታ ክልል ጥሰው በመግባት የራስ ፎቶ(ሰልፊ) ሲነሱ ነበር፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply