የተከሰከሰው አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ወደ ፈረንሳይ ተወሰደ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባው ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ሲበር ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 737-8 ማክስ የበረራ ቁጥር ET 302 አውሮፕላን መረጃ ሳጥን በፈረንሳይ አገር እንዲመረመር ዛሬ ወደ ፓሪስ መወሰዱን ኢትዮጵያ አየር መንገድ በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

ጀርመን የመረጃ ሳጥኑን እንድትመረምር ተጠይቃ ሶፍትዌሩ እንደሌላት በመግለፅ ጥያቄውን ሳትቀበል መቅረቷ ተገልፆ ነበር ትናንት።

የመረጃ ሳጥኑ ወደ ፓሪስ የሄደው በአለም አቀፉ አቪዬሽን አደጋ ምርመራ ቢሮ በሚመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ነው።
በአደጋው 157 ሰዎች ሞተዋል።

BBC

Share.

About Author

Leave A Reply