የተወዳጁ “ጸሀዬ ደመቀች” መዝሙር ዜማና ግጥም ደራሲ አቶ ሰለሞን ሰንደቁ ናቸው” ሰርጸ ፍሬ ስብሀት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

እኚህ ሰው፤ አቶ ሰሎሞን ታደሰ ሰንደቁ ይባላሉ። ልጅነታችንን ያደመቀችልንን፣ “ፀሐዬ ደመቀች” የተሰኘችውን የምንጊዜም ምርጥ የሕጻናት መዝሙር፣ ዜማና ግጥም የደረሱ ባለሙያ ናቸው።

መዝሙሩን የዘመሩት-የዝዋዮቹ “የዐብዮታዊት ኢትዮጵያ የሕጻናት አምባ”- ሕጻናት ዜማ እና ግጥሙን የደረሱት እና ያስዘመሯቸው እኚህ ሰው እንደነበሩ ያውቃሉ።

ኾኖም፣ በተለያዩ ጊዜያት፤ የዚህ መዝሙር “ደራሲ” እየተባሉ የተለያዩ ግለሰቦች ስም ሲጠቀስ ነበረ።

ዕድሜ ለሙዚቀኛ ሰሎሞን ሲሳይ (በሕጻናት አምባው ያደገ እና የአክሱማይት ባንድ ሳክስፎኒስት የነበረ) ለእኚህ ባለሙያ ባለማወቅ የነፈግነውን የፈጠራ ባለመብትነት እንድናርም ረድቶናል።

አቶ ሰሎሞን ታደሰ ሰንደቁ በአሁኑ ወቅት በካናዳ ኑሯቸውን የደረጉ ሰው ናቸው።

በዚህ አጋጣሚ፣ “ፀሐዬ ደመቀች”ን በተመለከተ፣የብዙዎቻችንን ስህተት ያረመውን ሙዚቀኛ ሰሎሞን ሲሳይን ከልብ አመሰግናለሁ።

(ሰርጸ ፍሬ ስብሀት)

Share.

About Author

Leave A Reply