የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምክንያት ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰራተኞቹ በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ የሰራተኛ አያያዝ፣ የምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ መናር የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ወ.ኪዳን ሰራተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ሰራተኞቹ ያቀረቡትን ችግር ለመፍታት በማወያየት ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ከሰዓት በኃላ የግንባታ ተቋራጩን ጨምሮ በሚደረግ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply