የንግድ ባንክና የልማት ባንክ የብድር ፖሊሲና አሠራር ለውጥ ተደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረዥምና የመካከለኛ ጊዜ የፕሮጀክት ብድሮች መስጠት በማቆም የሥራ ማስኬጃ ብድሮች ብቻ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ የፕሮጀክት ብድሮች እንዲሰጥ የተላለፈው ውሳኔ ታጠፈ፡፡ ውሳኔው ከሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈርሞ በወጣው ደበዳቤ እንደተገለጸው፣ ካሁን ቀደም የነበረው ውሳኔ ቀርቶ በቀድሞ አሠራር እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት ባለሀብቶች ከሁለቱም ባንኮች የፕሮጀክት ብድር ማግኘት ይችላሉ፡፡

በብሔራዊ ባንክ ገዥ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በፋይናንስና በአወቃቀር እንደገና በመጠናከር ይህንን ተልዕኮ መወጣት የሚችልበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ፣ የሁለቱም ባንኮች አሠራር ቀድሞ በነበረው እንዲቀጥል የተወሰነ መሆኑን አስታውቃለሁ፤›› ይላል፡፡

ምንጭ፤ ሪፖርተር

Share.

About Author

Leave A Reply