የአማራና ትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርች በክልሉ የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮችን በሰለም እንደሚካሄዱ አረጋገጡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል በየክልሎቻቸው የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች ሰለማዊ ሆነው እንደሚካሄዱ አረጋገጡ።

ርዕሰ መስተዳድሮቹ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ጋር በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ባሕር ዳር ላይ በተደረገው ውይይት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ውድድሮች ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የክልሉ ህዝብና መንግስት ፍላጎት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እንዳይከሰት በትኩረት እንደሚሰሩም አቶ ገዱ አረጋግጠዋል።

የስፖርት አመራሮቹ መቀሌ ላይ በነበራቸው ውይይትም የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው፤ በክልሉ የሚካሄዱ የስፖርት ዉድድሮች በተለመደዉ የእንግዳ አቀባበል ባህል መሠረት ለማስተናገድ የክልሉ ህዝብና መንግስት ዝግጁ መሆናቸዉን እንዳረጋገጡ የዘገበው የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ነው።

Share.

About Author

Leave A Reply