የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው ዛሬ ጥር 04/2011 ዓ.ም

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከሰጠው መግለጫ ተቀንጭቦ የቀረበ
1. የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣የመከላከያ ሚኒስትሯና ኤታማዦር ሹሙ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጡ እንጠይቃለን፡፡

2. ከሰሞኑ ገንዳኋና ኮኪትን ጨምሮ ራሳቸውን የቅማንት ኮሚቴ ነን ብለው የሚጠሩ የትሕነግ/ሕወኃት አሽከሮችን ውንብድና ወቅት መከላከያ ሰራዊቱ ከሕግ ውጭ ወደ ፀጥታ ማስከበር በመግባት ላደረሰው ግድያ ይቅርታ እንዲጠይቅና ለተጎጂ ቤተሰቦችም ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን፡፡

3. በሁለቱም አጋጣሚዎች ትዕዛዝ ያስተላለፉ፣ በወንጀሉ የተሳተፉና ወንጀሉን ለመሸፋፈን በሕዝባችን ላይ ተጨማሪ ቁጣን የቀሰቀሱ የመከላከያ አመራሮችና አባላት ለሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

4. መከላከያ ሰራዊቱ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ መዋቅሮች ሳይጠይቁት ወደ መደበኛ የፀጥታ ማስከበር ስምሪት እንዳይገባና የአገር ዳር ድንበርን የመጠበቅ ዋነኛ ተልዕኮው ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ የአገር መከላከያ በፍፁም የግል ድርጅት ጠባቂ መሆን እንደሌለበትም በጽኑ እናምናለን፡፡

5. የመካላከያ መዋቅሩና ሰራዊቱ ከትሕነግ/ሕወኃት አማራ-ጠል አስተምህሮ ዛሬም ድረስ እንዳልተላቀቀ በፈፀማቸው ፀረ-ሕዝብ ድርጊቶች የተረጋገጠ ስለሆነ እንዳዲስ ኢንዶክትሪኔሽን እንዲሰራለትና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በእኩል ዓይን ወደ ማየት እንዲሸጋገር እንጠይቃለን፡፡

የኢፌዲሪ መንግሥት ጥያቄዎቻችን በአስቸኳይ ምላሽ በመስጠት ፍትኅን ማስፈን ካልቻለ አልያም ፍትኅን ለማስፈን ፍላጎት ካላሳየ አብን መላውን አማራ በማንቀሳቀስ ተፈጥሯዊ መብቱን እንዲያስከብር የሚያስተባብር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በድጋሚ በመከላከያ ሰራዊት ተጨፍጭፈው ሕይወታቸው ባለፉ ወገኖቻችን ሞት እናዝናለን፡፡ የቆሰሉትም በቶሎ እንዲያገግሙ ምኞታችንን እየገለጽን፤ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ህዝባችን መጽናናትን በመመኘት መላው አማራው ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ አንድነቱን እንዲያፀና ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply