የአማራ ክልል ጥፋትም ሆነ ልማት የሚወሰነው በእኛው ነው- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“የአማራ ክልል ጥፋትም ሆነ ልማት የሚወሰነው በእኛው ነው” አሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው።

ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ለአማራ ክልል ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ነው ይህንን ያሉት።

አቶ ገዱ በማብራሪያቸው፥ “በአማራ ክልል ሰላም እንዳይሰፍንና የህግ የበላይነት ተጥሶ ስርዓት አልበኝነት እንዳይነግስ የደገፍነው ለውጥ እንዲጠፋ የሚፈልግ የውጭ ሀይል የለም” ብለዋል።

“የክልሉ ልማትም ሆነ ጥፋቱ የሚወሰነው በእኛው ነው” ብለዋል አቶ ገዱ በማብራሪያቸው።

በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ሰላም እንዲናጋ ‹‹ህወሀት ምክንያት ሊሆን አይችልም” ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፥ መወቀስም መሞገስም ካለበት በክልሉ ነው ብለዋል።

ከመጠን በላይ በበዛ ጥላቻ የአማራ ክልልን ለማመስ የሚደረገው ጥረት መልሶ ራሱን ወደጥፋት የሚያመራ ድርጊት ነውም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ እንደገለጹት፥ የአማራ ክልል ሰላም እንዲደፈርስ የብአዴን የቀድሞ አመራሮች ምክንያት ሊሆኑ አይችሉም፤ እነዚህ ሰዎች የሚችሉትን ሰርተዋል፤ እነዚህ ሰዎች ለሰላም እንጂ ጥላቻን አያስቡም ብለዋል።

“ዛሬ ላይ በክልሉ ሰላምን የሚያናጋ የውጭ ሀይል የለም ያሉት አቶ ገዱ፥ አሁን ላይ ሁሉም ነገር ክፍት፤ ፖለቲካዎ መታገያዎች ዝግጁ ናቸው ብለዋል።

ደብረ ማርቆስ ላይ የተከሰተው ብጥብጥ ራስን በራስ የማጥፋት እንቅስቃሴ ነው ነው ያሉት አቶ ገዱ እጅን መቀሰር የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ አይደለንም ብለዋል።

“የክልሉ ህዝብ ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፤ በተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ሰላምን ከፈለግን፤ ሰላምን ማደፍረስ ሳይሆን በሰከነ መንገድ ሰላምን በማምጣት የሁላችን ድርሻ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት 5 ኛ ዙር 3 ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎ እንደቀጠለ ነው።

ፋና

Share.

About Author

Leave A Reply