የአምባሳደር ዳዊት ዮሐንስና ዘሪሁን ረታ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አገራቸውን ለበርካታ ዓመታት በዲፕሎማትነት ያገለገሉት የቀድሞው አፈ ጉባኤ አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ አስከሬን ግብዓተ መሬት ተፈፀመ፡፡ስርዓተ ቀብሩ በዛሬው እለት እሁድ ጥር 26 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ7:30 በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርሰቲያን ተፈጸሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ተገኝተው የአበባ ጉን ጉን አስቀምጠዋል።በተጨማሪም በርካታ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሰራ ባልደረቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ ዜና አገራቸውን ለበርካታ ዓመታት በዲፕሎማትነት ያገለገሉት አምባሳደር ዘሪሁን ረታ የቀብር ስነ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርሰቲያን ተፈጽሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነና የመ/ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሰራ ባልደረቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ እና አምባሳደር ዘሪሁን ረታ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡ ምንጭ:- ኢቢሲ

Share.

About Author

Leave A Reply