የአንድ ዓመት ሴት ልጁን ከጣሪያ ላይ የወረወረው አባት ፍርድ ቤት ቀረበ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከአንድ ሳምንት በፊት የአንድ ዓመት ሴት ልጁን ከጣሪያ ላይ የወረወረው ደቡብ አፍሪካዊው አባት በህጻን ላይ ጥቃት በመሰንዘር በሚል ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ቀረበ።

ክሱ የግድያ ሙከራ ከሚለው ጥቃት በሚል ዝቅ ተደርጎለታል።

የ38 ዓመቱ ጎልማሳ ሴት ልጁን ከጣሪያ ላይ የወረወረው ፖርት ኤሊዛቤት ተብላ በምትጠራ ከተማ ያለፈቃድ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለማፈረስ የወጣውን ህግ በመቀውም ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነበር።

የአከባቢው መገናኛ ብዙሃኖች አባት ልጁን ከጣሪያ ላይ ሲወረውር የሚያሳየውን ምስል ተቀባብለውታል።

ፖሊስ ህጋዊ አይደሉም ያላቸውን ከ150 በላይ ደሳሳ ጎጆዎችን ሲያፈርስ ነበር።

አባት ልጁን ከጣሪያ ላይ የወረወረበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም ልጁን ጣሪያ ላይ ይዞ ከወጣ ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ የወረወራት ሲሆን ልጅቱ ምንም ጉዳት ሳይደርስባት በፖሊስ እቅፍ ላይ አርፋለች።

ምንም ጉዳት ያላስተናገደችው ህጻን አሁን ከእናቷ ጋር እንደምትገኝ ፖሊስ አስታውቋል።

የዋስ መብት የተከለከለው አባት ፍርዱን ለመቀበል ለፊታችን ሰኞ ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

Share.

About Author

Leave A Reply