የአይቀሬው ጦርነት ምልክቶች እና ዝግጅቶች፣ ወታደራዊ ቅኝት (Military Surveillance) በራያ!(ደጀኔ አሰፋ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ዛሬ በራያ ወረዳዎች ያልተለመደ ድባብ የተስተዋለበት እና የጦርነት ሽታ በግልፅ የሸተተበት ዕለት ነበር ተብሏል። ይህ ድባብ ደርግ ወደመጨረሻ ዘመን የነበረበት የድንግዝግዝ ወቅትን የሚያስታውስ ነውም ተብሏል። የልዩ ሃይሉ ቁጥር ከወትሮው በተለየ በአላማጣ በመሆኒና ኮረም መጨመሩ የተሰማ ሲሆን ከሁሉም ግን በአላማጣ ከተማ የልዩ ሃይሉ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ታውቋል።

ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ጀምሮ በቡድን በቡድን እየሆኑ ሽርጣቸውን እንደተከናነቡ አስፋልቱን ተከትለው ወደላይ እና ወደታች ይዘዋወሩ እንደነበር የተሰማ ሲሆን በመንገድ ዳር ተቀምጠው ጥቃቅን ንግድ (Pity Trade) የሚያካሂዱ በቆሎ ጠብሰው የሚሸጡ ፣ የተቀቀለ እንቁላል የሚሸጡ ሰዎችን “መሽቷል ወደቤት ግቡ” የሚል ትዕዛዝ ይሰጡም ነበር ተብሏል። ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ገደማም የመብራት ሃይል ስቴሽን ከሚገኝበት ከወደ ጅሃን አካባቢ የጥይት ድምፅ በተደጋጋሚ መሰማቱም ተረጋግጧል።

ከዚህ ደስ ከማይል ድባብ በተጨማሪ በራያ ዋጃ ጥሙጋ የትህነግ የወታደራዊ ቅኘት ቡድን ዛሬ ተሰማርቶ ውሏል። ቡድኑ ኮለኔል ብርሃነ (በቅፅል ስሙ አገው) የተባለ የቀድሞ ሰራዊት አባል የሚመራ ሲሆን መቶ አለቃ ሻምበል አባይ (ሻምበል የሰውየው ስም ማዕረጉ ደግሞ መቶ አለቃ የሆነ የመሆኒ ተወላጅ) ፣ ሻለቃ ትኩ እና መ/አለቃ ብርሃነ የሚባል የልዩ ሃይሎች አሰልጣኝ የቅኝት ቡድኑ አባላት ነበሩ ተብሏል። የቅኝት ቡድኑ መንገድ መሪ የቦረኑ ተወላጅ አርብሴ ፈንታ መሆኑም ታውቋል።

በሶስት መኪኖች የመጣው ይህ የቅኝት ቡድን በቀዳሚነት የጥሙጋ ኮረብታ (ጋሪያ) ጫፍ ላይ በመውጣት በአራቱም አቅጣጫ የቦታውን ወታደራዊ እና ስትራቴጅክ ጠቀሜታ መቃኘቱ የተሰማ ሲሆን የቡድኑ አመጣጥም ትህነግ ላሰበው አይቀሬ #ጦርነት የያዛቸውን ስትራቴጅክ ቦታዎች ለማጠናከር እና አዳዲስ ስልታዊ ቦታዎችንም ለመቀየስ እንደሆነ ግልፅ ነው ተብሏል። ቡድኑ የቅኝት ጉዞውን ቀጥሎ ወደተለያዩ የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች ያደረገ ሲሆን ሙኻ ሌንጫ ፣ ሰሌን ውሃና መሰል ቦታዎችን ከወታደራዊ ጠቀሜታቸው አንፃር ተዘዋዉሮ ቃኝቷል። ጦርነቱ ከተጀመረ ትህነግ መጀመሪያ ማጥቃት የሚፈልገው የቆቦ ፣ የሮቢትና የጎብየ ህዝብን ለመሆኑ ፍንጭ ሰጭ ነውም ተብሏል።

እንግዲህ በትህነግ በኩል ይህ ሁሉ የጦርነት ዝግጅት እና የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመ አንድም እንቅስቃሴ ከፌደራል መንግስትም ይሁን ከአማራ ክልል በኩል አለመታየቱ የራያ ህዝብን ግራ አጋብቷል። ምናልባትም የፌዴራል መንግስት የራያን ህዝብ እንደ ህዝብ ላይቆጥር አለያም ከትህነግ ጋር የተማማለበት ነገር ሊኖር ይችላል የሚል ስጋትን አጭሯል።

ያም ሆነ ይህ ግን የራያ ህዝብ ራሱን ለመከላከል ከወዲሁ መዘጋጀቱ የግድ ይሆናል። ከዚህ በኋላ ያለውንም ጊዜ ለአይቀሬው ጦርነት ከመዘጋጀት አንፃር የእያንዳንዷን ቀን ውሎ መፈተሽ ይኖርበታል። የእህል ዝግጅት ፣ የግቢ ውስጥ ምሽግ ቁፋሮ፣ አስፈላጊ መሳሪያዎችን መግዛትና ማደራጀት እንዲሁም የአካባቢን መውጫና መግቢያ ጥሩ አድርጎ መቃኘት ያሻል። ያልተደራጁ ወጣቶች በዙሪያቸው ካሉ ወገኖች ጋር ዛሬውኑ መደራጀት ግድ ይላቸዋል። መደራጀት ሃይል ነው!!! ያልተደራጀ ኃይል መከላከልም ሆነ ማሸነፍ አይችልም!!! እውቀት ማለት መደራጀት ነው!!! መደራጀት ወቅቱ የሚጠይቀው ትንሹ ግዴታ ነው!

(ደጀኔ አሰፋ)

Share.

About Author

Leave A Reply